1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኢትዮጵያ ፖለቲካዊ ጉዞና የኢዴፓ አቋም

ሰኞ፣ ሰኔ 7 2002

እየተቃወመ-የመደገፉን፣እየደገፈ-የመቃወሙን መርሕ-ሰወስተኛ አማራጭ-ይሉዋል-ኢደፓ።መርሁ በርግጥ አማላይ ብጤ ነዉ።በምርጫዉ ግን ኢዴፓን-ከዜሮ-ሥሌት ዜሮ ዉጤት አለማዉጣቱ እንጂ ዚቁ

https://p.dw.com/p/NqXz
ምርጫዉምስል DW

14 06 10


የኢትዮጵያዉያን ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኢዴፓ-ባጭሩ) ከኢትዮጵያ ተቃዋሚ ፓርቲዎች በርግጥ አንዱ ነዉ።ፓርቲዉ መንግሥትን ከመቃወሙ-እኩል ከብዙዎቹ ተቃዋሚ ፓርቲዎች አፈንግጦ-አንዳድ መንግት መርሆችን መደገፍ፣ ተቃዋሚዎችን ከመደገፉ ባልተናነሳ-ሁኔታ መቃወም ከጀመረ ዉሎ አደረ።እየተቃወመ-የመደገፉን፣እየደገፈ-የመቃወሙን መርሕ-ሰወስተኛ አማራጭ-ይሉዋል-ኢደፓ።መርሁ በርግጥ አማላይ ብጤ ነዉ።በምርጫዉ ግን ኢዴፓን-ከዜሮ-ሥሌት ዜሮ ዉጤት አለማዉጣቱ እንጂ ዚቁ።የኢዴፓ መሪ አቶ ልደቱ አያሌዉ እንግዳችን፣ የፓርቲዉ መርሕ ትኩረታችን የኢትዮጵያ ፖለቲካዊ ጉዞ መድረሻችን ነዉ ላፍታ አብራችሁኝ ቆዩ።


ኢንጂነር ሐይሉ ሻዉል-የመላዉ ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት መኢአድ-ባጭሩ መስራችና መሪ።

አቶ ስዬ አብረሐ የቀድሞዉ የኢሕአዴግ ታጋይ፥ የኢትዮጵያ መከላከያ ሚንስትርና አሁን የኢትዮጵያ አንድነት ለፍትሕና ለዴሞክራሲ (አንድነት ባጭሩ) ፓርቲ ከፍተኛ አመራር አባል።

አቶ ቡልቻ ደመቅሳ የኦሮሞ ፌደራሊስት ዲሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ኦፍዴን) መስራችና መሪ።የሁሉም ፓርቲዎች ተቃዋሚዎች ናቸዉ።ሁሉም በግንቦት አስራ-አምስቱ ምርጫ ተካፋዮች ነበሩ።ሥለ ምርጫዉና ዉጤቱ የሁሉም አቋም ተመሳሳይ ነዉ።

የኢትዮጵያዉያን ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኢዴፓ)ም እንደ ሁሉም ፓርቲዎች ሁሉ ተቃዋሚ ፓርቲ ነዉ።እንደ ሁሉም ፓርቲዎች ሁሉ በግንቦት አስራ-አምስቱ ምርጫ ተካፋይ ነበር።ሥለ ምርጫዉ ዉጤትና የኢትዮጵያ ፖለቲካዊ ሁኔታ ግን የኢዴፓ መስራችና መሪ አቶ ልደቱ አያሌዉ ከሌሎቹ ተቃዋሚ ፖለቲከኞች ጋር የሚስማሙት ግማሽ ድረስ ነዉ።

አንድነትና ኦፍዴንን የሚያስተናብረዉ የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ (መድረክ ባጭሩ) የምርጫዉን ሒደት ነፃ፥ ትክክለኛና ሠላማዊ ያደርገዋል የተባለዉን የፓለቲካ ፓርቲዎች የምርጫ ሥነ-ምግባር ደንብን አልፈረመም።መኢአድ ግን ፈርሟል።ኢዴፓም ፈርሟል።መድረክ የምርጫዉን ዉጤት ዉድቅ አድርጎ ምርጫዉ እንዲደረገም ጠይቋል።መኢአድም እንዲሁ።

ኢዴፓ ግን ምርጫዉ እንዲደገም አልጠየቀም።አቶ ልደቱ።
ኢዴፓ እንደሌሎቹ ተቃዋሚዎች እየተቃወመ የሌሎቹን ተቃዋሚዎች አቋም ሙሉ በሙሉ ያለ መጋራቱ መሠረት አቶ ልደቱ እንደሚሉት ሰወስተኛ አማራጭ የሚለዉ መርሑ ነዉ።ይሕ መርሁ ደግሞ በምርጫዉ ጥሩ ዉጤት አምጥቶለታል።
የወደፊቱ የኢትዮጵያ ፖለቲካዊ ጉዞም አቶ ልደቱ እንደሚያምኑት ሠላማዊ፥ ከገዢዉ ፓርቲ ጋር በሚደረግ ድርድር፥ እና ተቃዋሚዎች ወደ አንድነት በሚያመጣ ዉይይት ላይ የተመሠረተ፥ ተቋማትን በመቀየር ላይ ያተኮረ መሆን አለበት።
የዚያ ሰዉ ብሎን ለመታዘብ ያብቃን።ደሕና አምሹ።

ነጋሽ መሐመድ

ሒሩት መለሠ