የኢትዮጵያ ፖለቲከኞች ዉዝግብ ምርጫና የአሜሪካ ኤምባሲ
ሐሙስ፣ መጋቢት 17 2001ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ መንግሥት እና ተቃዋሚ ፓርቲዎች በመጪዉ አመት ሊደረግ ሥለታቀደዉ ምርጫ ገና ከወዲሕ የገጠሙት ዉዝግብ እንደቀጠለ ነዉ።ዉዝግቡ ቢቀጥልም የሐገሪቱ ምርጫ ቦርድ ሥለ ምርጫዉ ዝግጅትና ሒደት ለማወያየት የፖለቲካ ፓርቲ ተጠሪዎችን ለስብሰባ ጋብዟል።በአዲስ አበባ የዩናይትድ ስቴትስ ኤምባሲ ባለሥልጣናት በበኩላቸዉ የአንድነት ለፍትሕና ለዲሞክራሲ ፓርቲ መሪዎችን ባለፈዉ ሳምንት አነጋግረዉ ነበር።ታደሰ እንግዳዉ ዝር ዝር ዘገባ ልኮልናል።
ታደሰ እንግዳዉ
ነጋሽ መሐመድ