1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኢትዮጵያ ፖለቲከኞቸ ድርድር፥ ዉዝግብና ሸምግልና

ዓርብ፣ ኅዳር 4 2002

ስምንት የፖለቲካ ፓርቲዎችን ከሁለት ታዋቂ ግለሰቦች ጋር የሚያስተናብረዉን ተቃዋሚ ፓርቲ ከገዢዉ ፓርቲ ጋር ለማግባባት ፕሮፌሰር ኤፍሬም ኢስሐቅ የሚመሩት የሐገር ሽማግሌዎች ጓድ ሽምግልና ጀምሯል

https://p.dw.com/p/KWTQ
አዲስ አበባምስል picture alliance/dpa

የኢትዮጵያ ገዢ የፖለቲካ ፓርቲ ኢሕአዴግና ከተቃዋሚዎቹ መካካል ሰወስቱ ከዚሕ ቀደም ባፀደቁት የምርጫ ሕገ-ደንብ ላይ ሲደራደሩ የሰነበቱት ከሥልሳ የሚበልጡ የፖለቲካ ፓርቲዎች ሕጉን ከማሻሻያ ጋር መቀበላቸዉን አስታወቁ።ፓርቲዎቹ ትናንት ባወጡት መግለጫ እንዳሉት የተስማሙበትን ሠነድ የሐገሪቱ ምርክር ቤት እንዲያፀድቀዉ ይልኩታል።በድርድሩ ያልተካፈለዉን እና ስምንት የፖለቲካ ፓርቲዎችን ከሁለት ታዋቂ ግለሰቦች ጋር የሚያስተናብረዉን ተቃዋሚ ፓርቲ ከገዢዉ ፓርቲ ጋር ለማግባባት ፕሮፌሰር ኤፍሬም ኢስሐቅ የሚመሩት የሐገር ሽማግሌዎች ጓድ ሽምግልና ጀምሯል።የአዲስ አበባዉ ወኪላችን ታደሰ እንግዳዉ ዝር ዝር ዘገባ አለዉ

ታደሰ እንግዳዉ
ነጋሸ መሐመድ
አርያም ተክሌ