1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኢትዮጵያ ፕሬዝዳትና ተቃዋሚ ፖለቲከኞች

ማክሰኞ፣ መስከረም 28 2006

የሰማዊ ፓርቲ ምክትል ሊቀመንበር አቶ ሥለሺ ፈይሳ እንደሚሉት ደግሞ የአዲሱ ፕሬዝዳት አዲስ ነገር በራሳቸዉ ተንቀሳቅሳዉ እንግዳ መቀበል የሚችሉ መሆናቸዉ ነዉ።ዶክተር ሙላቱ ቻይና እና ዩናይትድ ስቴትስ የተማሩ፥ ኢሕአዴግ ሥልጣን ከያዘበት ጊዜ ጀምሮ በምክትል ሚንስትርነት፥ በሚንስትርነት፥ በአፈ-ጉባኤነት፥ በአምባሳደርነት ያገለገሉ ናቸዉ።

https://p.dw.com/p/19wHe
***Für mögliche Ergänzungen der Karte, wie z.B. andere Sprachen, zusätzliche Orte oder Markierungskreuz, wenden Sie sich bitte an infografik@dw-world.de (-2566), Außerhalb der Bürozeiten an bilder@dw-world.de (-2555).*** DW-Grafik: Per Sander 2011_03_10_Laender_Prio_A_B

የኢትዮጵያ የሕዝብ ተወካዮች እና የፌደሬሽን ምክር ቤት አባላት ትናንት የወደፊቱን የኢትዮጵያ ፕሬዝዳት መርጠዋል።ዶክተር ሙላቱ ተሾመን።ዶክተር ሙላቱ ትናንት ዘመነ-ሥልጣናቸዉ ካበቃዉ ከፕሬዝዳት ከግርማ ወልደ ጊዮርጊስ በዕድሜም፥ በጤናም፥ በትምሕርትም የተሻሉ በመሆናቸዉ እንዳዶች የተሻለ ሥራ ይሰራሉ የሚል ተስፋ አላቸዉ።ተቃዋሚ ፖለቲከኞች እንደሚሉት ግን የአዲሱ ፕሬዝዳት አዲስነት ከአካላዊ ብቃት ያለፈ አይደለም።የገዢዉ ፓርቲ የኢሕአዴግ ከፍተኛ ባለሥልጣን በመሆናቸዉና የሐገሪቱን ዉስብስብ ችግሮች ለመፍታት የሚተክሩት የለም።ነጋሽ መሐመድ አስተያየቶቹን አሰባስቧል።

ዶክተር ሙላቱ ተሾመ አዲስ ፕሬዝዳንት እንጂ አዲስ ፖለቲካኛ አይደሉም።የፕሬዝዳትነቱ ሥልጣንም ከወጋዊ ወይም ከተምሳሌታዊነት ያለፈ አይደለም።በዚሕም ሰበብ የዓለም አቀፉ የፀጥታ ጥናት ተቋም ባልደረባ አቶ ሐሌሉያ ሉሌ እንደሚሉት ከአዲሱ ፕሬዝዳት አዲስ ነገር አይጠበቅም።ተስፋ ግን ትንሽም ቢሆን አይጠፋም።

የተቃዋሚዉ የኦሮሞ ፌደራል ኮንግሬስ ሊቀመንበር ዶክተር መረራ ጉዲና የኦሮሞ ሕዝብ እንደ ብዛትና ሥፋቱ በኢትዮጵያ ፖለቲካ የተሻለ ሥልጣን ማግኘት አለበት በማለት ይከራከራሉ።በሳቸዉ አገላለፅ «በቁመቱ ልክ»።የብሔር ፖለቲካን የሚያቀነቅነዉ ኢሕአዴግ ሕገ-መንግሥት ካስፀደቀ ወዲሕ ያስመረጣቸዉ ሰወስቱም ፕሬዝዳንቶች የኦሮሞ ተወላጆች ናቸዉ።ይሕ የነዶክተር መረራን ተደጋጋሚ ጥያቄ-የመመለሱ ምልክት ይሆን?

የመላዉ ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) ፕሬዝዳት አቶ አበባዉ መሐሪም አዲሱ ፕሬዝዳት በኢትዮጵያ ፖለቲካ የተምሳሌትነት አስተዋፅኦ ያደርጋሉ የሚል ተስፋ ቀርቶ አመራረጣቸዉ ራሱ ሕገ-መንግሥቱን የጠበቀ ነዉ-ማለት አይቻልም።


የሰማዊ ፓርቲ ምክትል ሊቀመንበር አቶ ሥለሺ ፈይሳ እንደሚሉት ደግሞ የአዲሱ ፕሬዝዳት አዲስ ነገር በራሳቸዉ ተንቀሳቅሳዉ እንግዳ መቀበል የሚችሉ መሆናቸዉ ነዉ።

ዶክተር ሙላቱ ቻይና እና ዩናይትድ ስቴትስ የተማሩ፥ ኢሕአዴግ ሥልጣን ከያዘበት ጊዜ ጀምሮ በምክትል ሚንስትርነት፥ በሚንስትርነት፥ በአፈ-ጉባኤነት፥ በአምባሳደርነት ያገለገሉ ናቸዉ።ሐምሳ ሰባት ዓመታቸዉ።

Demonstration der Semayawi-Partei ("Blaue Partei"), 22.09.2013 Addis Ababa, Äthiopien Thema: Die junge Semayawi-Partei hat sich an die Spitze der Potestbewegung in Addis Ababa gesetzt. *** Copyright: DW/September 2013
ምስል DW

ነጋሽ መሐመድ

ሸዋዬ ለገሠ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ