የኢትዮጵያ ፍርድ ቤት ዉሎ
ማክሰኞ፣ መጋቢት 18 2004ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሰወስተኛ ወንጀል ችሎት በአሸባሪነት የተከሰሱ ፖለቲከኞችንና ጋዜጠኞችን የመከላከያ ምስክሮች ዛሬም ለሁለተኛ ቀን ሲያደምጥ ዉሏል።የተቃዋሚዉ የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ (አንድነት) ከፍተኛ ባለሥልጣን በሆኑት በአቶ አንዱ አለም አራጌ መዝገብ ከተከሰሱት ሃያ አራት ተጠርጣሪዎች መካካል ጋዜጠኛ እስክድር ነጋ ይገኝበታል።ዛሬ አዲስ አበባ ላስቻለዉ ፍርድ ቤት ተቃዉሟቸዉን ካሰሙት ተከሳሾች አንዱ ደግሞ ከተጠለሉበት ከሱዳን ስደተኞች ሠፈር ታፍነዉ ወደ ኢትዮጵያ እስር ቤት መጋዛቸዉን አስታዉቀዋል።የአዲስ አበባዉ ወኪላችን ታደሰ እንግዳዉ ዝር ዝር ዘገባ አለዉ።
ታደሰ እንግዳዉ
ነጋሽ መሐመድ
አርያም ተክሌ