የኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ የሥልጣን ውዝግብ
ሰኞ፣ ታኅሣሥ 16 2010ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኢዴፓ) የአመራርነት ሥልጣኑ ይገባኛል በሚል የአባላት ክርክር ይታመስ ይዟል። አቶ አዳነ ታደሰ በአንድ በኩል እንዲሁም እስካሁን በፕሬዝዳንትነት የሚታወቁት ዶ/ር ጫኔ ከበደ በተቃራኒው ሆነው የይገባኛል ውዝግቡን ይመሩታል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በበኩሉ አቶ አዳነ ታደሰ የተመረጡት ምልዓተ-ጉባኤ ሳይሟላ በመሆኑ የድርጅቱን ማሕተም ሊጠቀሙ አይገባም ብሏል። የቀድሞው የፓርቲው ፕሬዝዳንት አቶ ልደቱ አያሌው በወገናቸው የምርጫ ቦርድን ቅሬታ አዳምጠን በዛሬው ዕለት በሕገ-ደምቡ መሰረት አቶ አዳነ ታደሰ ፕሬዝዳንት አድርገን መርጠናል እያሉ ነው።
ጌታቸው ተድላ ወልደጊዮርጊስ
ነጋሽ መሐመድ