የኢትዮጵያ የፕሬስ ነፃነት እና CPJ
ዓርብ፣ ጥቅምት 18 2009ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ መንግሥት አዲስ በደነገገዉ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አማካይነት ወትሮም ያመነመነመዉን የፕሬስ ነፃነትን ይበልጥ እየደፈለቀዉ መሆኑን ዓለም አቀፉ የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች ድርጅት እስታወቀ።CPJ በሚል ምሕፃረ-ቃል የሚጠራዉ የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች ድርጅት በተለያዩ ሐገራት ያለዉን የጋዜጠኝነት ነፃነትን ባጠናበት ዘገባዉ እንዳለዉ ኢትዮጵያ መገኛኛ ዘዴዎችን በመዝጋትና ጋዜጠኞችን በማሰር የመጀመሪያዉን ደረጃ ከያዙት ሐገራት ተርታ ተሰልፋለች።የዋሽግተን ዲሲዉ ወኪላችን መክብብ ሸዋ ዝርዝር ዘገባ ልኮልናል።
መክብብ ሸዋ
ነጋሽ መሐመድ
ሸዋዬ ለገሰ