የኢትዮጵያ የፀጥታው ምክር ቤት ተለዋጭ አባልነት
ረቡዕ፣ ሰኔ 22 2008ማስታወቂያ
ኢትዮጵያ በተመድ የፀጥታ ጥበቃ ምክር ቤት የተለዋጭ አባልነት መቀመጫ ማግኘቷ በአገር ውስጥ ከሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ድርጅቶች እና የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች በኩል ልዩ ልዩ አስተያየቶች እየተሰነዘሩበት ነው። የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዴሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ(«መድረክ» በአጭሩ) ኢትዮጵያ ይህን ቦታ ማግኘቷን ፋይዳ ቢስ ሲለው፤ የኢትዮጵያ ራዕይ ፓርቲ ኢራፓ ደግሞ ኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብቶችን አያያዝን ለማሻሻል ትጠቀምበት ብሏል። የሰብዓዊ መብቶች ጉባኤ ሊቀመንበር በበኩላቸው በዙር የሚደርሰውን ይህን ቦታ ኢትዮጵያ ማግኘቷ ትርጉም የለውም ብለዋል ።አስተያየቶቹን ያሰባሰበው የአዲስ አበባው ዘጋቢያችን ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሄር ዝርዝሩን ልኮልናል ።
ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሄር
ኂሩት መለሰ
ነጋሽ መሐመድ