1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኢትዮጵያ የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ ፈተና

ሰኞ፣ ግንቦት 22 2008

የኢትዮጵያ የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ ፈተና ሾልኮ ወጥቶ በማህበራዊ ድረ-ገጾች ከተሰራጨ በኋላ የትምህርት ሚኒስቴር ፈተናውን አቋርጧል።

https://p.dw.com/p/1IxKO
Äthiopien Zerihun Deresa in Addis Abeba
ምስል DW/Y. Gebreegziabher

[No title]

የኢትዮጵያ የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ ፈተና ሾልኮ ወጥቶ በማህበራዊ ድረ-ገጾች ከተሰራጨ በኋላ የትምህርት ሚኒስቴር ፈተናውን አቋርጧል። የኢትዮጵያ ትምህርት ሚኒስቴር በፌስ ቡክ ማህበራዊ ድረ-ገጽ ባሰራጨው መረጃ 254,000 ለሚሆኑ የ12ኛ ክፍል ተፈታኞች የተዘጋጀው እና «ኮድ 14 የሚባለው የእንግሊዝኛ ፈተና ከነመልሱ ሞራል በጎደላቸው ሰዎች አማካኝነት በተላያዩ ድረ ገፆች የተለቀቀ በመሆኑ» እንዲቋረጥ መደረጉን አስታውቋል። የኦሮሞ ተቃውሞ አራማጆች በማህበራዊ ድረ-ገጾች በክልሉ ተቀስቅሶ በነበረው ተቃውሞ የመማር ማስተማር ሒደቱ ተስተጓጉሎ የነበረ በመሆኑ « ትምህርት ሚኒስቴር ይህን ፈተና ሰርዞ ለተማሪዎች በቂ ጊዜ ሰጥቶ አዲስ ፈተና እንዲያዘጋጅ ታስቦ » ፈተናው መሰራጨቱን ጽፈዋል።

የኢትዮጵያ ፈተናዎች ድርጅት ፈተናው እንዴት እንደወጣ በማጣራት እርምጃ እንደሚወስድ አስታውቋል። የአዲስ አበባው ወኪላችን ዮሐንስ ገብረእግዚዓብሔር ተፈታኝ ተማሪዎችንና የፈተናዎች ድርጅት ኃላፊን በማነጋገር ዘገባ ልኮልናል።

በዚህ ጉዳይ ላይ የኦሮሞ ተቃውሞን በቅርበት የሚከታተለውን አራማጅ ወይም አክቲቪስት ገረሱ ቱፋ አስተያየቱን አካፍሎናል።

ዮሐንስ ገብረእግዚዓብሔር

እሸቴ በቀለ

አርያም ተክሌ