የኢትዮጵያ የኑሮ ውድነትና የዋጋ ግሽበት
እሑድ፣ መስከረም 9 2008ማስታወቂያ
ካለፈው ዓመት አጋማሽ አንስቶ በኢትዮጵያ የሸቀጦች በተለይም የምግብ ነክ ምርቶች ዋጋ በፍጥነት እየጨመረ በመሄድ ላይ ይገኛል። ባለፉት ሦስት ወራት ደግሞ የተወሰኑ ምግብ ነክ ሸቀጦች እስከዛሬ ታይቶ በማይታወቅ ደረጃ ዋጋቸው ንሯል። ለዋጋ ጭማሪው በምክንያትነት ከሚነሱት ውስጥ የአቅርቦትና ፍላጎት አለመመጣጠን አንዱ ነው። አንዳንድ የኤኮኖሚ ባለሞያዎች ደግሞ ችግሩ የሃገሪቱ የኤኮኖሚ ፖሊሲ ላይ ነው ያለው ይላሉ። መንግሥት ችግሩን የሚያባብሱት ስግብግብ የሚላቸው ነጋዴዎች ናቸው ሲል ይከሳል።
ኂሩት መለሰ
ማንተጋፍቶት ስለሺ