1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኢትዮጵያ የሰብአዊ መብት ይዞታ

ሰኞ፣ መጋቢት 9 2005

ምንም እንኳን በኢትዮጵያ ህገ መንግሥት ሰብአዊና ዲሞክራሲያዊ መብቶች ቢዘረዘሩም እነዚህን መብቶች በሚጥሱና በሚሸረሽሩ ሌሎች ህጎች ምክንያት ተግባራዊ ሊሆኑ አለመቻላቸውን የሃገር ውስጥም ሆነ የዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች ድርጅቶች እንዲሁም ተቃዋሚ የፖለቲካ ድርጅቶች በየጊዜው ስሞታ ያቀርባሉ ።

https://p.dw.com/p/17zQv

በኢትዮጵያ ሰብአዊና ዲሞክራሲያዊ መብቶች እንደማይከበሩ አለም አቀፍ የመብት ተከራካሪ ድርጅቶች የውጭ መንግሥታት የሐገር ውስጥ ተቃዋሚ ፓርቲዎችና መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች በተለያዩ ጊዜያት የሚያወጧቸው ዘገባዎች ያስረዳሉ ። የኢትዮጵያ መንግሥት ባለሥልጣናት ግን የሰብአዊ መብት አያያዝ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተሻሻለ መምጣቱን ነው የሚናገሩት ። ምንም እንኳን በኢትዮጵያ ህገ መንግሥት ሰብአዊና ዲሞክራሲያዊ መብቶች ቢዘረዘሩም እነዚህን መብቶች በሚጥሱና በሚሸረሽሩ ሌሎች ህጎች ምክንያት ተግባራዊ ሊሆኑ አለመቻላቸውን የሃገር ውስጥም ሆነ የዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች ድርጅቶች እንዲሁም ተቃዋሚ የፖለቲካ ድርጅቶች በየጊዜው ስሞታ ያቀርባሉ ። እነዚህ ወቀሳዎች የሚቀርቡበት መንግሥት በቅርቡ «ብሔራዊ የሰብአዊ መብቶች የድርጊት መርሃ ግብር » ያለውን ሠነድ አዘጋጅቷል ።በድርጊት መርሃ ግብሩ ፋይዳ ና በኢትዮጵያ የሰብአዊ መብት ይዞታ ላይ እንግዶችን ጋብዘን አወያይተናል ።

ሂሩት መለሰ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ