1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአቶ መለስ ዓለም መግለጫ

ሐሙስ፣ ኅዳር 28 2010

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ እየሩሳሌምን የእስራኤል ዋና ከተማ አድርገው እውቅና በመስጠታቸው ላይ የኢትዮጵያን አቋም የተጠየቁት የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አቶ መለስ ዓለም መንግሥት የሁለት መንግሥታት መፍትሄን እንደሚደግፍና የመካከለኛው ምሥራቅ ችግርም በሰላም እንዲፈታ እንደሚፈልግ ተናግረዋል።

https://p.dw.com/p/2oy3D
Äthiopien Meles Alem Sprecher Außenministerium
ምስል DW/G. Tedla

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መግለጫ

ኢትዮጵያ ለእሥራኤል ፍልስጤም ውዝግብ የሁለት መንግሥታት የመፍትሄ እርምጃን እንደምትደግፍ ገለጸች። የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ እየሩሳሌምን የእስራኤል ዋና ከተማ አድርገው እውቅና በመስጠታቸው ላይ የኢትዮጵያን አቋም የተጠየቁት የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አቶ መለስ ዓለም መንግሥት የሁለት መንግሥታት መፍትሄን እንደሚደግፍና የመካከለኛው ምሥራቅ ችግርም በሰላም እንዲፈታ እንደሚፈልግ ተናግረዋል። ቃል አቀባዩ ዛሬ በሰጡት መግለጫ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርን በአዲስ መልክ ስለ ማዋቀር ፣  በሊቢያ እና በሳውዲ አረብያ ስለሚገኙ የኢትዮጵያ ስደተኞች ጉዳይም ማብራሪያ ሰጥተዋል። ጋዜጣዊ መግለጫውን የተከታተለው የአዲስ አበባው ዘጋቢያችን ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ ዘገባ አለው። 
ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ 
ኂሩት መለሰ
ነጋሽ መሐመድ