1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኢትዮጵያ ወታደሮች፧ በሞቅዲሹ ለተቸገሩ ሶማሌዎች እህል ማከፋፈላቸው፧

ሐሙስ፣ ግንቦት 7 2000

በሶማልያ መዲና በመቅዲሹ የሚገኙ የኢትዮጵያ ወታደሮች፧ በትናንቱ ዕለት፧ ከመደበኛ ተልእኮአቸው ውጭ፧ ለተቸገሩ የከተማይቱ ኑዋሪዎች እህል በማከፋፈል ተግባር ላይ ተሠማርተው መታየታቸውን የዜና አውታሮች አስታወቁ።

https://p.dw.com/p/E0Xj
አንድ ኢትዮጵያዊ ወታደር፧ ሶማልያ ውስጥ፧ በፀጥታ አጠባበቅ ግዳጅ ላይ፧
አንድ ኢትዮጵያዊ ወታደር፧ ሶማልያ ውስጥ፧ በፀጥታ አጠባበቅ ግዳጅ ላይ፧ምስል AP
መቅዲሹ ውስጥ፧ ባይኒሌ በተሰኘው ወረዳ፧ ኢትዮጵያውያኑ ወታደሮች፧ 500 ገደማ ለሚሆኑ ሰዎች፧ 400 ኩንታል ማሽላ ለማከፋፈል ነው የተሠማሩት። እንደዜና አውታሮቹ ዘገባ ከሆነ፧ ወታደሮቹ ከደመወዛቸው አዋጥተው ነው በተሠማሩት የከተማ ክፍል ለሚገኙ ችግረኞች ኑዋሪዎች እርዳታ የሰጡት።......
የሮይተርስ ዜና አገልግሎት ድርጅት ጋዜጠኞች እንደዘገቡት፧ በቀድሞው የሶማልያ የጦር ኃይሎች ሠፈር ለተሰበሰቡ በመቶዎች ለሚቆጠሩ በረሃብ ለተጠቁ ሶማሌዎች፧ ለሶማሊያ የሽግግር መንግሥት ጋሻ ለመሆን የተሠማሩት ኢትዮጵያውያኑ ወታደሮች፧ እርዳታ ሰጥተዋል። የከተማይቱ ኑዋሪዎች፧ በረሃብ የተጠቁት በእህል ዋጋ መናርና ቸርቻሪ ነጋዴዎችም፧ ዶላር ካልሆነ እህል ሸማቾች የሚሰጧቸውን አሮጌ የሶማልያ የወረቀት ገንዘብ አንቀበልም፧ እያሉ በማስቸገራቸው ጭምር መሆኑ ነው የተነገረው። አብዲፋታኅ አብዲካዲር የተባሉ የተጠቀሰው የከተማ ክፍል ኑዋሪ፧.........
«ይህ ታይቶ የማይታወቅ ነው። የኢትዮጵያ ወታደሮች ሰዎች ላይ በመተኮስ ነበረ የሚታወቁት። ይህ የአሁኑ የበጎ ሐሳብ ተግባር በከተማው የመነጋገሪያ ርእስ ሆኗል። ህዝቡ፧ ምን ዓይነት መልእክት ለማስተላለፍ ፈልገው ይህን እንደሚያደርጉ፧ በመገረም ሆኗል የሚከታተለው« ሲሉ መናገራቸውም ተጠቅሷል። የእርዳታው ተሳታፊዎች ከሆኑት የኢትዮጵያ ሠራዊት አባላት መካከል አበራ በላቸው የተባለ ወታደር እንዲህ ይላል።
(ድምፅ)...........
የህዝቡ ችግር የቱንን ያህል አሳሳቢ እንደሆነ ትንሽ እንዲያብራራልኝም ጠይቄው........
«.....................«
የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት፧ እንደገለጸው ከሆነ ከሲሦ በላይ የሚሆነው የሶማልያ ህዝብ በውጭ እርዳታ መመካት ግድ ሆኖበታል። በተለይ በከተሞች ከሚኖረው ህዝብ መካከል በድህነት የተጎሳቆሉት፧ የዕለት ጉርስ የማግኘት ከባድ ችግር እንዳለባቸው ነው የሚነገረው። የሶማልያን የሽግግር መንግሥት ራሱን ችሎ በእግሩ እንዲቆም ለማብቃትም ሆነ የሶማልያን የሸሪያ ፍርድ ቤቶች ኅብረት ከሥልጣን ለማስወገድ የኢትዮጵያ ሠራዊት ሶማልያው ውስጥ ከገባ 17 ወር ገደማ ሆኗል። እስካሁን፧ አገሪቱ አልተረጋጋችም፧ ተቃውሞና ግጭትም ሊወገድ አልቻለም። በመሆኑም፧ ሁሉንም የአገሪቱ ድርጅቶች በማሳተፍ የፖለቲካ መፍትኄ እንዲገኝ የሚደረገውን ጥረትም በመቀጠል፧ ኢቡቲ ውስጥ በሳምንቱ ማለቂያ ላይ፧ የሶማልያን የሽግግር መግሥትና የተቃውሞውን ወገን ያሳተፈ የሰላም ውይይት ቢከፈትም፧ አሥመራ ውስጥ በስደት የሚገኙት የቀድሞው የሶማልያ ጦር ሠራሲት ኮሎኔል፧ የሸሪያ ፍርድ ቤቶች ኅብረት መሪ፧ ሼክ ሐሰን ዳሂር አዌስ አልደገፉትም። ከእርሳቸው ጋር ጉድኝት የፈጠረው ሆኖም በጉባዔው በመሳተፍ ላይ ያለው «የሶማልያ ዳግም ሐርነት« የተሰኘው ድርጅት ስብሰባውን ረግጦ ይወጣ ዘንድ በመጠየቅ ላይ ናቸው። አዌስ፧ ኢትዮጵያ ሶማልያን በኃይል ይዛላችና፧ በቅድሚያ መውጣት አለባት፧ ነው የሚሉት።