1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኢትዮጵያ ከሶማልያ መውጣት

ረቡዕ፣ ጥር 6 2001

ወደሶስት ሺህ የሚጠጉ የኢትዮጵያ ወታደሮች አሁንም ቀውስ ባላጣት በሶማልያ መዲና ሰሜናዊ ከፊል ከሚገኙ ሁለት ጦር ሰፈሮች ለቀው ወጡ።

https://p.dw.com/p/GYJf
የኢትዮጵያ ወታደር በኪስማዩ
የኢትዮጵያ ወታደር በኪስማዩምስል AP

እንደ ወራሪ ኃይል ይታዩ ለነበሩት ኢትዮጵያውያን ወታደሮች የሶማልያ የሽግግር መንግስት ደማቅ አሸኛኘት አድርጎላቸዋል። የሽግግሩ መንግስት ተቃዋሚ የሆኑት የሶማልያ ዳግም ነጻነት ለዘብተኛ ሙስሊሞችም ሚሊሺያዎች የኢትዮጵያ ወታደሮች የለቀቁዋቸውን ሰፈሮች ከሌሎች ተፎካካሪ ተቀናቃኞቻቸው ጋር ተዋግተው መያዛቸው ተገልጾዋል። አንዳንድ የዚሁ ኅብረት ከፍተኛ አባላት አሁን በምክር ቤቱ አፈ ጉባዔና ባለፈው ወር ስልጣናቸውን የለቀቁትን ፕሬዚደንት አብዱላሂ ዩሱፍን በተኩት በተጠባባቂ ፕሬዚደንት ሼክ አደን ማዶቤ የሚመራውን የሽግግር መንግስት ተቀላቅለዋል።