1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን መቀጣት፤

ረቡዕ፣ ጥር 15 2005

የአፍሪቃ እግር ኳስ ኮንፈደሬሽን፤ (CAF)ደቡብ አፍሪቃ ውስጥ በመካሄድ ላይ ባለው የአፍሪቃ ዋንጫ ውድድር፣ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ደጋፊዎች ከእንግዲህ እስከ ውድድሩ ፍጻሜ የጋጠ ወጥነት ተግባር ካልፈጸሙ 5ሺ አለበለዚያ 10 ሺ ዶላር ቅጣት

https://p.dw.com/p/17QT6
ምስል DW

በፌደሬሽኑ ላይ የሚጣልበት መሆኑን አስታውቋል። ከ 31 ዓመታት ወዲህ ፤ ወደ አፍሪቃ የእግር ኳስ ዋንጫ ውድድር የተመለሰችው ኢትዮጵያ፣ ባለፈው ሰኞ ከዛምቢያ ጋር ባደረገችው ግጥሚያ ተመልካቾችን ያረካ፤ የእግር ኳስ ሐያስያንንም ያስደነቀ እንቅሥቃሴ በማሳየት 1-1 መለያየቷ የሚታወስ ነው። ስለተጣለው ቅጣትና ቀጣዩ ጨዋታ ፣ የፌደሬሽኑን አባልና የእስፖርት ጋዜጠኛ አቶ መላኩ አየለን በማነጋገገር በማነጋገር ተከታዩ ዘገባ ተጠናቅሯል።ኢትዮጵያ ከትናንት በስቲያ ደቡብ አፍሪቃ ውስጥ ኔልስፕሪዩት በተባለችው ከተማ፣ በእምቦምቤላ ስታዲዬም፣ ከዛምቢያ ጋር ባደረገችው ግጥሚያ ፣ በዚያ ተገኝተው ለቡድኑ ሞቅ ያለ የሞራል ድጋፍ የሰጡት ኢትዮጵያውያን፣ እንዲያ ማበረታታቸው ቢያሥመሰግናቸውም፤ አንዳንዶች በፈጸሙት ህገ-ወጥ ድርጊት ፌደሬሽኑ ቅጣት ተጥሎበታል። የቅጣቱ ሰበብ በእርግጥ ምንድን ነው? የፌደሬሽኑ አባልና የእስፖርት ጋዜጠኛ አቶ መላኩ አየለ---በዚያው በእምቦቤላ ስታዲዬም ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ሞቅ ያለ ድጋፍ የሰጡ ብቻ ሳይሆን «አሉ»ያሏቸውን «የሰብአዊ መብት ጥሰቶች» በ T-SHIRT አማካኝነት ያንጸባረቁ እንደነበሩ የጠቆሙ መረጃዎችም አሉ።የተጣለውን ቅጣት በተመለከተ ፣ አንድ የአግር ኳስ ፌደሬሽን ይመለከተኛል ብሎ ለመቀበልም ላለመቀበል፣ ደጋፊዎች የሚባሉትን እርሱም ሆነ CAF በምን መለኪያ ነው የሚያውቋቸው!?በተጠቀሰው ስታዲዬም በመገኘት ጨዋታውን ከተመለከቱት ደጋፊዎች መካከል በአዲስ አበባና በደቡብ አፍሪቃ የሚኖሩ ሁለት ኳስ አፍቃሪዎች እንዲህ ብለዋል---።

Africa Cup Fans Äthiopien vs Sambia
ምስል DW
Africa Cup Zuschauer Äthiopien vs Sambia
ምስል DW

ስለቀጣዩ ግጥሚያ ዝግጅት---አቶ መላኩ አየለ---።

ተክሌ የኋላ

ሸዋዬ ለገሰ