የኢትዮጵያ አየር መንገድ የጭነት ማከማቻ ሕንፃ ግንባታ
ሰኞ፣ የካቲት 16 2007ማስታወቂያ
የሕንጻ ገንቢው ተቋራጭ በኢትዮጵ የሚገኝ የአንድ የኢጣልያ ኩባንያ ሲሆን፤ ግንባታው የሚካሄደውና በውስጡ ለሚገኙ ቁሳቁሶች አቅርቦት በፈረንሳይና ጀርመን ከሚገኙ ባንኮች ብድር የተገኘ መሆኑ ተገልጿል። በሁለት ፈረቃ የሚሠሩት ሕንጻዎች፣ በዓመት ከአንድ ሚሊዮ ን 200ሺ ቶን በላይ የጭነት ቁሳቁስ የሚከማችበትና በየበረራ አቅጣጫዎቹ አገልግሎት የሚያበረክት ይሆናል። የአይሮፕላን ጭነት ማከማቻው ሕንጻ በግዙፍነቱ በአፍሪቃ የመጀመሪያው ፣ በዓለም አቀፍ ደረጃም ከታላላቆቹ አንዱ ሊባል እንደሚችል ተብራርቷል ።
ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ
ተክሌ የኋላ
ኂሩት መለሰ