1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኢትዮጵያ አየር መንገድ አዲስ ሕግ

ማክሰኞ፣ የካቲት 25 2006

አየር መንገዱ ወይም ሕጉን ያወጣዉ የኢትዮጵያ የገቢዎችና የጉሙርክ ባለሥልጣን የየሠራተኞቻቸዉን ጤና ለመጠበቅ እስከ ዛሬ የቆዩበት ምክንያትም ግልፅ አይደለም። መስሪያ ቤቶቹ አሁን ለመከልከላቸዉ ሁለተኛ ያሉት ምክንያት ግን አላቸዉ።

https://p.dw.com/p/1BJaK
ምስል Reuters

የኢትዮጵያ አየር መንገድ አዉሮፕላኖቹ አሮጌ ልብሶችና የግል ቁሳቁሶች አሳፍረዉ ወደ ኢትዮጵያ እንዳጉዙ አገደ።የአየር መንገዱ ባለሥልጣናት በቅርቡ ባሠራጩት ደብዳቤ እንዳስታወቁት በተለይ በፕላስቲክ በርሚል ታሽገዉ ወደ ኢትዮጵያ የሚገቡ አሮጌ አልባሳትና ቁሳቁሶች የጉምሩክ ፈታሾችን ጤና እያወኩ ነዉ።ባለሥልጣናቱ እንደሚሉት ያገለገሉ ወይም አሮጌ አልባሳትና ቁሳቁሶች ከማሸጊያቸዉ በተጨማሪ ሐገሪቱን «የቁሻሻ መጣያ» እያደረጓት ነዉ።በዚሕም ምክንያት ያገለገሉ አልባሳትና ቁሳቁሶች ከየካቲት ሃያ-ሁለት ጀምሮ ጀምሮ ወደ ኢትዮጵያ መግባት አይችሉም።


የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለየቅርንጫፎቹ ያሰራጨዉ ደንባቤዉም በሥልክ ያነጋገርናቸዉ ባለሥልጣኑም እንደሚሉት ያገለገሉ ወይም አርጌ አልባሳት ከየካቲት ሃያ-ሁለት ሁለት ሺሕ ስድስት ጀምሮ ወደ ኢትዮጵያ እንዳይገባ ታግዷል።በሁለት ምክንያት።ምክንያት አንድ፥

ይላሉ አቶ ፍፁም አባዲ-የአየር መንገዱ የጭነት ወይም የካርጎ አስተዳደር ሐላፊ ናቸዉ።
ያገለገሉ አልባሳት የሚታሸግበት የፕላስቲክ በርሜል እስካሁን በሠራተኞች ላይ ያደረሰዉ የጤና ችግር እንዴትነት፥ ደረጃዉም ሆነ የተጎዳዉ ሠራተኛ ማንነት አልተጠቀሰም።

አየር መንገዱ ወይም ሕጉን ያወጣዉ የኢትዮጵያ የገቢዎችና የጉሙርክ ባለሥልጣን የየሠራተኞቻቸዉን ጤና ለመጠበቅ እስከ ዛሬ የቆዩበት ምክንያትም ግልፅ አይደለም።መስሪያ ቤቶቹ አሁን ለመከልከላቸዉ ሁለተኛ ያሉት ምክንያት ግን አላቸዉ።እንደገና አቶ ፍፁም።

በሌላ ማሸጊያ ቢሆንስ ለምሳሌ በሻንጣ፥ በካርቶን ወይም በሳጥን ማስገባት ይቻል ይሆን።«ይቻላል» ይላሉ አቶ ፍፁም ግን አሮጌ መሆን የለበትም።ሥለዚሕ በግልፅ ቋንቋ ያገለገሉ አልባሳትና የግል ቁሳቁሶችን ወደ ኢትዮጵያ ማስገባት አይቻልም።

Boeing 787 Ethiopian Airlines
ምስል Reuters

ነጋሽ መሀመድ

ሂሩት መለሰ