የኢትዮጵያ አንድነት ዴሞክራሲያዊ ድርጅት መግለጫ
ረቡዕ፣ ሰኔ 3 2007ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ አንድነት ዴሞክራሲያዊ ድርጅት የተሰኘዉ ተቃዋሚ ፓርቲ ባለፈዉ ግንቦት 16 የተደረገዉ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ነፃና ፍትሃዊ አልነበረም ሲል አስታወቀ ።የፓርቲው ፕሬዝዳንት አቶ አድማሱ ኃይሉ ከዶቼቬለ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ምርጫው ነፃና ዲሞክራሲያዊ ስላልሆነ ፓርቲያቸው እንደማይቀበለው ተናግረዋል ።አቶ አድማሱ እንዳሉት በዕጩዎች ምዝገባ በምርጫ ቅስቀሳና በምርጫውም ወቅት የፓርቲያቸው አባላት እጩዎቻቸውና ታዛቢዎቻቸው ወከባና እንግልት ደርሶባቸዋል ። ከዛሬ 16 ዓመት በፊት የተመሰረተው የኢትዮጵያ አንድነት ዴሞክራሲያዊ ድርጅት በ1997ቱና በ2002ቱ ምርጫም ተካፍሏል ። አቶ አድማሱን ስቱድዮ ከመግባቴ በፊት በስልክ አነጋግሬያቸዋለሁ ።
ኂሩት መለሰ
ነጋሽ መሀመድ