የዘንድሮው ውጤት ከቀደሙት ውድድሮች አኳያ ቀንሷል።
እሑድ፣ ነሐሴ 14 2009ማስታወቂያ
ቀዳሚዎቹ ስመጥር አትሌቶች አስከብረዋቸዉ ከቆዩት ርቀቶች ዘንድሮ አልተገኙም። በተቃራኒዉ በ5000 ሜትር ለዓመታት ተወስዶ የነበረዉ ክብር ዘንድሮ ተመልሷል። ያም ሆኖ ግን ብዙዎች የጠበቁትን ያህል በዉጤቱ አልረኩም። አትሌቶቹም እንዲሁ። ብቸኛዉ የኢትዮጵያ መታወቂያ የሩጫ ስፖርት አሁን ድሉ የቅርብ ተፎካካሪ ወደሆነች ወደጎረቤት ኬንያ ፊቱን ያዞረ መስሏል ወይም አዙሯል። የኢትዮጵያ አትሌቲክ ፌዴሬሽን ዉስጠ ምስጢሩም በሚያዉቁት ባለድል አትሌቶች መመራት ከጀመረ አንድ ዓመት ቢሆነዉ ነዉ። የአትሌቲክስ ስፖርቱ አሁን ወዴት እያመራ ነዉ? ዉጤት መራቁስ ለምን? ዶይቸ ቬለ ያደረገውን ውይይት ማድመጥ ይችላሉ።
ሸዋዬ ለገሠ
ልደት አበበ