1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሂዩመን ራይትስ ዋች አስተያየት

ረቡዕ፣ ጥቅምት 2 2009

ሚስ ሌስሊ ሌፍኮ ለኢትዮጵያ ወቅታዊ ችግር መፍትሄ ካሏቸው መካከል በህገ ወጥ መንገድ በፀረ ሽብር ህግ የታሰሩትን ተቃዋሚዎች መፍታት እና ለሞቱት እና ለቆሰሉት ካሳ መስጠት ይገኝበታል ።

https://p.dw.com/p/2R9hs
Human Rights Watch - Leslie Lefkow EINSCHRÄNKUNG
ምስል Human Rights Watch

Beri Wash.Rxn HRW / Ausnahmezustand Äthiopien - MP3-Stereo

ኢትዮጵያ ባለፈው ሳምንት የደነገገችው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በጣም እንደሚያሳስበው ዓለም ዓቀፉ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅት ሂዩመን ራይትስ ዋች አስታወቀ ።የድርጅቱ የአፍሪቃ ጉዳዮች ሃላፊ  ሚስ ሌስሊ ሌፍኮ  በሰጡት አስተያየት አዋጁ መሠረታዊ ሰብዓዊ መብቶችን ሊገድብ  ይችላል የሚል ስጋት እንዳላቸው ተናግረዋል ። የኢሬቻን በዓል ለማክበር በሄዱበት በቢሾፍቱ የሞቱት ሰዎች ጉዳይ በዓለም ዓቀፍ ገለልተኛ ወገን እንዲጣራም ሃላፊዋ ጠይቀዋል ። ለኢትዮጵያ ወቅታዊ ችግር መፍትሄ ካሏቸው መካከል በህገ ወጥ መንገድ በፀረ ሽብር ህግ የታሰሩትን ተቃዋሚዎች መፍታት እና ለሞቱት እና ለቆሰሉት ካሳ መስጠት ይገኝበታል ። ያነጋገራቸው የዋሽንግተን ዲሲው ዘጋቢያችን መክብብ ሸዋ ዝርዝሩን ልኮልናል።

መክብብ ሸዋ
ኂሩት መለሰ  
ነጋሽ መሐመድ