1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኢትዮጵያ ተቃዋሚዎች ስሞታና የመንግሥት መልስ

ማክሰኞ፣ የካቲት 17 2001

የኢትዮጵያ መንግሥት ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲ መሪዎች በመንግሥትና በገዢዉ ፓርቲ ላይ ያሰሙትን ወቀሳና ሥሞታ አንድ የመንግሥት ከፍተኛ ባለሥልጣን አጣጥለዉ ነቀፉት።

https://p.dw.com/p/H0Yy
ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊምስል dpa

ባለፈዉ ሳምንት የጋራ ሕብረት ወይም ግንባር ለመመስረት የተስማሙት የተቃዋሚ ፓርቲዎች መሪዎች እንደሚሉት መንግሥት መሪዎቻቸዉን፥ አባላቶቻቸዉና ደጋፊዎቻቸዉን ያላግባብ ያስራል፥ ከሥራ ያፈናቅላል፥ ነፃ መገናኛ ዘዴዎችን ያፍናል።የመገናኛ ወይም የኮሙኒኬሽን ጉዳይ ሚንስትር ደኤታ አቶ አርሚያስ ለገሠ እንደሚሉት ግን የተቃዋሚዎቹ ክስና ወቀሳ በመረጃ አልተደገፈም።ታደሰ እንግዳዉ ዝር ዝር ዘገባ አለዉ።