1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ መግለጫ

ሐሙስ፣ ግንቦት 27 2007

የፖለቲካ ፓርቲዎች የምርጫውን ውጤት አንቀበልም ማለታቸው አሳፋሪ ነው ሲሉ ሃላፊዎቹ በመግለጫቸው አስታውቀዋል ። ከምርጫው በፊት ለቦርዱ የቀረቡ ቅሪታዎች እልባት ማግኘታቸውን የተናገሩት ሃላፊዎቹ በምርጫው ቀን ግን ለቦርዱ የቀረበ ቅሬታ እንደሌለም ገልፀዋል ።

https://p.dw.com/p/1FbrC
Äthiopien NEBE Presskonferenz in Addis Abeba
ምስል DW/Yohannes G/Egziabhare

[No title]

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የተራዘመው የቦንጋ ምርጫ ሰኔ 7 ፣ 2007 ዓም እንደሚካሄድ አስታወቀ ። የቦርዱ ሃላፊዎች ዛሬ በሰጡት መግለጫ የዚህ ምርጫ ሪፖርትም ሰኔ 15 ቀን ይፋ በሚደረገው አጠቃላይ ዘገባ ውስጥ ተካቶ እንደሚቀርብ ተናግረዋል ። ከዚህ ሌላ የፖለቲካ ፓርቲዎች የምርጫውን ውጤት አንቀበልም ማለታቸው አሳፋሪ ነው ሲሉ ሃላፊዎቹ በመግለጫቸው አስታውቀዋል ። ከምርጫው በፊት ለቦርዱ የቀረቡ ቅሪታዎች እልባት ማግኘታቸውን የተናገሩት ሃላፊዎቹ በምርጫው ቀን ግን ለቦርዱ የቀረበ ቅሬታ እንደሌለም ገልፀዋል ። ጋዜጣዊ መግለጫውን የተከታተለው የአዲስ አበባው ዘጋቢያችን ዮሐንስ ገብረ እግዚዘብሔር ዝርዝር ዘገባ አለው ።

ዮሐንስ ገብረ እግዚ እግዚዘብሔር

ኂሩት መለሰ

ሸዋዬ ለገሠ