የምርጫ ቦርድ መግለጫ
ማክሰኞ፣ ጥር 5 2007ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ዛሬ ከቀትር በኋላ የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት መኢአድን የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ አንድነትንና ሰማያዊ ፓርቲን የሚመለከት መግለጫ ሰጥቷል ። ቦርዱ በዚሁ መግለጫው የውስጥ ችግሮቻቸውን ጉባኤ ጠርተው እንዲፈቱ ማሳሰቢያ ለሰጣቸው ለመኢአድና ለአንድነት ፓርቲዎች የተባሉትን እንዲያደርጉ ተጨማሪ ጊዜ እንደተሰጣቸው አስታውቋል ። በዚሁ መግለጫ ይቅርታ የመጠየቂያ የጊዜ ገደብ ያስቀመጠለት ሰማያዊ ፓርቲ ማስጠንቀቂያ እንደተሰጠውም ገልጿል ። ጋዜጣዊ መግለጫው ላይ የተገኘው የአዲስ አበባው ዘጋቢያችን ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔርን ዝርዝሩን በስልክ ጠይቄው ነበር ።
ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር
ኂሩት መለሰ
ተክሌ የኋላ