1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የጀርመኑ ድርጅት ትችት

ዓርብ፣ ነሐሴ 6 2008

ኢትዮጵያ ዉስጥ በተለያዩ አካባቢዎች የተካሄደዉን ሰላማዊ ሰልፍ ለመበታተን የመንግሥት የፀጥታ ኃይል በወሰደዉ የኃይል ርምጃ የበርካቶች ህይወት ጠፍቶ አዉሮጳም ሆነ ጀርመን ፈጥነዉ አላወገዙም ሲል አንድ የጀርመን መንግሥታዊ ያልሆነ ተቋም ወቀሰ።

https://p.dw.com/p/1JhOB
Ulrich Delius
ምስል Gesellschaft für bedrohte Völker

[No title]

በመላዉ ዓለም ለጥፋት አደጋ ለተጋለጡት ሕዝቦች የሚታገለዉ ገዜልሻፍት ፉይር በድሮህተ ፎልከር የተባለዉ ድርጅት የአዉሮጳ ኅብረትም እና የጀርመን መንግሥት እስካሁን ድረስ ምንም ሳይናገሩ ዝም በማለታቸዉ ድርጅቱ ባወጣዉ መግለጫ እንዲህ አይነቱ አቋም ያሳዝናል፤ ያሳፍራል ሲል ተቸ። የድርጅቱ ኃላፊ ለዶቼ ቬለ በሰጡት ቃለ ምልልስ ከአዉሮፓ ኅብረት የወጣዉ መግለጫ ጀርመን ሃገር ዉስጥ ባለፉት ቀናት በጋዜጦች እና ቴሌቪዝን በዚህ ጉዳይ ላይ የቀረቡ ዘገባዎችን የቃኘዉ የበርሊኑ ዘጋቢያችን ይልማ ኃይለ ሚካኤል የድርጅቱን ኃላፊ በማነጋገር ተከታዩን ዘገባ ልኮልናል።

ይልማ ኃይለ ሚካኤል

ሸዋዬ ለገሠ

ኂሩት መለሰ