1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

Merga Yonas Bula
ሰኞ፣ መስከረም 8 2010

በኢትዮጵያ ሶማሌና በኦሮሚያ ክልል ድንበሮች መካከል በተከሰተዉ ግጭት ምክንያት ቁጥራቸዉ በዉል ያልተወቀ ሰዎች ከሁለቱም ወገኖች ተገድለዋል። ከ55,000 በላይ ኦሮሞዎች ከቀያቸዉ እንደተፈናቀሉ ዘገባዎች ያመለክታሉ።

https://p.dw.com/p/2kDm0
Äthiopien Stadt Jijiga
ምስል DW/T. Waldyes

Ethiopia-Somali&Oromia Reg. St. Conflict - MP3-Stereo

የሁለቱ ክልል ርዕሰ መስተዳደሮች ትላንት በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ሠላምና መረጋጋትን ለማስፈን ቃል ገብተዋል። የኢትዮጵያ ሶማሊ ርዕሰ መስተዳደር አቶ አብዲ ሙሀመድ ኡመር በሁለቱ ክልል «ፀጥታና አመራር ምክንያት ወንድማማች የሆኑ ህዝብ ማጋጨት የለብንም» ብለዋል።

የኦሮሚያ ክልል ፕሬዝዳንት አቶ ለማ መገርሳ ጉዳዩ ከድንበር የዘለለና ያለዉ አዝማምያ ለአገርቱ አደገኛ መሆኑን ጠቅሰዉ፣ የህዝቡ መተሳሰር በምንም መልኩ መበላሸት የለበትም ሲሉ ተደምጠዋል።

ጠቅላይ ሚንስተር ሃይለማርያም ደሳለኝ ሁለቱንም ርዕሰ መስተዳደሮችን ትናት እንዳነጋገሯቸዉ ዘገባዎች ይጦቁማሉ። በዚህም መሰረት በሁለቱም ክልሎች የሚገኙ ዋና ዋና መንገዶችን ፌዴራል መንግስታት የፀጥታ ሃይሎች እንደሚቆጣጠሩ፣ የፌዴራል መንግስት የጦር መሳርያ እንደሚያስፈታና ሕይወት ባጠፉ የፀጥታ ሃይላት ላይ ርምጃ እንደሚወሰድ ሚንስትሩ ትዛዝ መስጠታቸዉም ተዘግበዋል።

የክልሉ መንግስታት የገቡት ቃልና የፌዴራል መንግስት የያዘዉን እቅድ እንዴት እንደምመለከቱት የሰዎችን አስተያየት ተቀብለን ነበር። በአምቦ ዩኒቨርስቲ ወሊሶ ካምፓስ አስተማሪ የሆኑትና የድረ-ገፅ ፀሐፊዉ መምህር ስዩም ተሾመ መንግስት ሰላም የማሰፍን ግዴታ አለበት ይላሉ። ይሁን እንጅ በኦሮሚያ ክልል ሕብረተሰቡ እራሱን ከ«ልዩ ፖሊስ» ጥቃት ለመከላከል ከመጣሩ ዉጪ  የታጠቀ ሃይል እንደሌለ አቶ ስዩም ይናገራሉ።

Äthiopien Stadt Jijiga
ምስል DW/T. Waldyes

የፌዴራል ፀጥታ ሃይል ከመጀመርያዉ ጀምሮ አከባቢዉ ላይ ይገኛሉ የሚሉት ስማቸዉ እንዳይጠቅስ የጠየቁ አንድ የአዳማ ነዋሪ «መከላክያ ከልዩ ፖሊስ ጋር ወግኖ ወረራዉን አካሒዷል» ሲሉ ለዶይቼ ቬሌ ተናግረዋል። ትጥቅ ማስፈታት ከሆነ የተጠቀ ሃይል ከልዩ ፖሊስ ዉጭ ሌላ ሃይል የለም ይላሉ እኝ አስተያየት ሰጭ።

የሐገሪቱ የሰባዊ መብት ኮሚሺንና ቀይ መስቀል እስካሁን በቦታዉ ላይ እንዳልተገኙ የአዳማ ከተማ ነዋርዉ ይናገራሉ። የአለማቀፉ የሰባዊ መብት ተሟጋች (HRW) የአፍሪካ ጉዳዮች ከፍተኛ አጥኚ ፌሊክስ ሆርን ያለዉ ሁኔታ በጣም አሳሳብ ነዉ ካሉ በዋላ መንግስት የአለማቀፍ ርዳታ ድርጅት ወደ ቦታዉ እንዳይገቡ ማድረጉ አንዱ ችግር መሆኑን ለዶይቼ ቬሌ ተናግረዋል። የአጋርቱን ሰባዊ መብት ኮሚሺን «ይህን ጊጭት ከወራቶች በፍት ጀምሮ መመርመር ነበረበት። ግጭቱ ወደ ነበረበት ድረስ የመጓዝ ፊቃድና አቅም ነበረባቸዉ። አሁን ምን እንደምመረምሩም አለዉቅም፣» ያላሉ አጥኝዉ። «ግን ገለልተኛና ተቀባይነት ያለዉ ምርመራ እንደምያደርጉ ተስፋ አደርጋለዉ። ይህ ካልሆነ ግን መንግስት የማይወደዉን የአለማቀፍ ድርጅቶች ምርመራቸዉን ያካህዳሉ፣»ስሉም አክሎበታል።

በፌዴራልም ሆነ በክልሉ መንግስታት በኩል በጉዳዩ ላይ ተጨማር ማብራርያ እንድሰጡን ያደርገነዉ ሙከራ አልተሳካም።

መርጋ ዮናስ

ነጋሽ መሃመድ