1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኢትዮጵያ ስኳር ድርጅት

ማክሰኞ፣ ሚያዝያ 16 2004

የኢትዮጵያ ሱካር ኮርፖሬሽን ለሸንኮራ አገዳ ልማት እያለ ሰዎችን ያፈናቅላል፥ ታሪካዊና የእምነት ሥፍራዎችን ያፈርሳል፥ ለተፈናቃዮች ካሳ አይከፍልም የሚለዉን ወቀሳ አስተባበለ።

https://p.dw.com/p/14kLS
Äthiopisch-orthodoxe Mönche weilen in einer Felshöhle im Komplex der Felsenkirchen von Lalibela (Foto vom 18.11.2005). Diese Felsenkirchen in der Provinz Amhara im Norden des Landes gehören zu den wichtigsten Kunstwerken der Christenheit und zum UNESCO Weltkulturerbe. Die elf Kirchen und Kapellen des Komplexes sollen während der 40-jährigen Herrschaft König Lalibelas im 12./13. Jahrhundert in den weichen roten Tuffstein gehauen worden sein. Manche Reiseführer ziehen einen Vergleich zu Jordanien und sprechen vom afrikanischen Petra. Doch während dort nur die Fassaden aus Sandstein herausgearbeitet sind, so sind es in Lalibela freistehende Kirchen, zum Teil aus einem Stein gehauen. Foto Thomas Schulze +++(c) dpa - Report+++
ምስል picture alliance/dpa

በሚንስትር ማዕረግ የኮርፖሬሽኑ ሐላፊ አቶ አባይ ጸሐዬ ዛሬ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንደነገሩት መስሪያ ቤታቸዉ ለተፈናቃዮች ካሳ ይከፍላል።ታሪካዊና የእምነት ሥፍራዎችን አፍርሷል የሚለዉን ወቀሳና ትችት ግን አቶ አባይ አጣጥለዉ ነቅፈዉታል።ሁለት ነባርና አስር አዳዲስ የስኳር ፋብሪካዎችን እንዲያሰራና እንዲመራ የተቋቋመዉ መስሪያ ቤት ለሁለት ሺሕ አራት ዓመት ብቻ 20.24 ቢሊዮን ብር በጀት ተመድቦለታል።እስካሁን ግን በእቅዱ መሠረት አልሰራም።

ታደሰ እንግዳዉ

ነጋሽ መሀመድ

አርያም ተክሌ