የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ዘገባ እና የተመድ የሰብዓዊ መብት ምክር ቤት ምላሽ
ሰኞ፣ ሚያዝያ 16 2009ማስታወቂያ
ተቃውሞዎቹን በተመለከተ የማጣራቱ ተግባር በአንድ ገለልተኛ አካል እንዲደረግ የተመድ እና የአውሮጳ ህብረት ጥያቄ ማቅረባቸው እና ጥያቄአቸው ከኢትዮጵያ መንግሥት በኩል ተቀባይነት አለማግኘቱም አይዘነጋም። ለዚህም የኢትዮጵያ መንግሥት ዠኔቭ የሚገኘው የተመድ የሰብዓዊ መብት ጽህፈት ቤት የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ያቀረበለትንየመጀመሪያ ዘገባ ተቀባይነት ያለው ነው ማለቱን እንደምክንያት ገልጿል። ስለዚሁ ጉዳይ የዋሽንግተኑ ወኪላችን መክብብ ሸዋ በዠኔቭ የሚመለከተውን ክፍል ባልደረቦች አነጋግሮዋል።
መክብብ ሸዋ
አርያም ተክሌ
ነጋሽ መሀመድ