የኢትዮጵያ ራዕይ ፓርቲ መግለጫ
ረቡዕ፣ ታኅሣሥ 17 2005ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ ራዕይ ፓርቲ የተባለው ተቃዋሚ ፓርቲ በመጪው ሚያዚያ በሚካሄደው የአዲስ አበባና የአካባቢ ምርጫ እንደሚሳተፍ አስታወቀ ። የፓርቲው መሪዎች ዛሬ በሰጡት መግለጫ እንዳሉት አብዛኛዎቹ ተቃዋሚ ፓርቲዎች በምርጫው ለመሳተፍ ብዙ ቅድመ ሁኔታዎችን ቢያስቀምጡም የራዕይ ፓርቲ ግን በምርጫው ለመሳተፍ መወሰኑን አስታውቀዋል ። መሪዎቹ በሰጡት መግለጫ የኢትዮጵያ መንግሥት በቅርቡ ሁለት ተጨማሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስሮችን መሾሙን ህገ መንግሥቱን የጣሰ በማለት ሲቃወሙት በየአካባቢው መስተዳደር የተለያዩ ምክንያቶች በመስጠት ቤቶች መፍረሳቸውን የዜግነትን መብት መጣስ ነው በማለት አውግዘውታል ።
ዮሐንስ ገብረ እግዚዘብሔር
ሒሩት መለሰ
ነጋሽ መሐመድ