1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኢትዮጵያ ሠፈራ መንደርና ሠብአዊ መብት

ማክሰኞ፣ ጥር 8 2004

የኢትዮጵያ መንግሥት ከሐገሪቱ ምዕራባዊ ግዛት በሺ የሚቆጠሩ ነዋሪዎችን ከየመኖሪያ ቀያቸዉ አፈናቀለ በማለት ሑዩማን ራይትስ ወች ወቀሰ።///በአለም አቀፍ ዜና አገልግሎት በኩል የደረሰን ዘገባ እንደሚያመለክተዉ የኢትዮጵያ መንግሥት ግን ይሕን የሁይማን ራትስ ወችን ዘገባ አጣጥሎ ነቅፎታል።

https://p.dw.com/p/13l6t
ካራቱሪ-ከዉጪ ኩባንዮች አንዱምስል DW/Schadomsky

የኢትዮጵያ መንግሥት ከሐገሪቱ ምዕራባዊ ግዛት በሺ የሚቆጠሩ ነዋሪዎችን ከየመኖሪያ ቀያቸዉ አፈናቀለ በማለት ሑዩማን ራይትስ ወች ወቀሰ።ዓለም አቀፉ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅት እንደሚለዉ መንግሥት በቅርቡ ከሁለት ሚሊዮን ሔክታር በላይ ለም መሬት ለዉጪ ባለሐብቶች በሊዝ ለማኮናተር አቅዷል።ለዚሕ እቅዱ ስኬት ድርጅቱ እንደሚለዉ በርካታ ሕዝብን ከየመኖሪያ አካባቢዉ እያነሳ ሌላ አካባቢ-እያሰፈረ ነዉ።የመብት ተሟጋቹ ድርጅት የመንግሥትን እርምጃ ሰብአዊ መብትን የሚጥስ በማለት አዉግዞታል።የለንደኑ ወኪላችን ድልነሳ ጌታነሕ ዝር ዝር ዘገባ አለዉ።

_______________________________________________________________-

በአለም አቀፍ ዜና አገልግሎት በኩል የደረሰን ዘገባ እንደሚያመለክተዉ የኢትዮጵያ መንግሥት ግን ይሕን የሁይማን ራትስ ወችን ዘገባ አጣጥሎ ነቅፎታል።አሶሽየትድ ፕረስ የጠቀሰዉ የኢትዮጵያ የፌደራል ጉዳዮች ሚንስትር ዶክተር ሺፈራዉ ተክለማርያም ለሁይማን ራይትስ ዋች የፃፉት ደብዳቤ የመብት ተሟጋቹ ድርጅትን ዘገባ «የተፈበረከና፥ ፖለቲካዊ አለማ ያለዉ ነዉ።የሚንስትሩ ደብዳቤ አክሎ እንዳመለከተዉ ሰዎች ተፈናቀሉ በተባለበት አከባቢ አዲስ መንደር የሠፈሩ ከሐምሳ ሺሕ በላይ ነዋሪዎች ያገኙትን ጥቅም ሑማይን ራይትስ ዋች ሆን ብሎ ዘልሎታል።ዘገባዉ እንደሚለዉ በጋምቤላ አካባቢ በተገነባዉ የሠፈራ መንደር የሚኖረዉ ሕዝብ ከቀለቡ የሚተርፍ አትክልትና ሰብል እያመረተ ነዉ።

ድልንሳ ጌታነሕ

ነጋሽ መሐመድ

አርያም ተክሌ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ