1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኢትዮጵያ ምርጫና የመገናኛ ዘዴዎች ሚና

እሑድ፣ ጥር 24 2007

የምርጫዉ ዝግጅት እና ሒደቱ በሚያነጋግርበት፤ ፓርቲዎችንና ምርጫ ቦርድን በሚያወዛግብበት መሐል ዓለም አቀፉ የመብት ተሟጋች ድርጅት ሑዩማን ራይትስ ዋች ባወጣዉ ዘገባ የኢትዮጵያ መንግሥት በነፃ መገናኛ ዘዴዎችና በጋዜጠኞች ላይ የሚያደርሰዉ ጫና እና በደል እየባሰ መምጣቱን በዝርዝ ዘግቧል

https://p.dw.com/p/1ETf8
ምስል DW

ኢትዮጵያ ዉስጥ በመጪዉ ግንቦት ለሚደረገዉ አጠቃላይ ምርጫ የፖለቲካ ፓርቲዎች ዝግጅት፤ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድና የተቃዋሚ ፓርቲዎች የገጠሙት ዉዝግብ እንደቀጠለ ነዉ።የምርጫዉ ዝግጅት እና ሒደቱ በሚያነጋግርበት፤ ፓርቲዎችንና ምርጫ ቦርድን በሚያወዛግብበት መሐል ዓለም አቀፉ የመብት ተሟጋች ድርጅት ሑዩማን ራይትስ ዋች ባወጣዉ ዘገባ የኢትዮጵያ መንግሥት በነፃ መገናኛ ዘዴዎችና በጋዜጠኞች ላይ የሚያደርሰዉ ጫና እና በደል እየባሰ መምጣቱን በዝርዝ ዘግቧል።ለዛሬዉ ዉይይታችን «የኢትዮጵያ ምርጫና የመገናኛ ዘዴዎች ሚና» የሚል ጥቅል ርዕስ ሰጥተነዋል።

የዘንድሮዉን ምርጫ፤ አሰልቺዉን የጋዜጠኞች ቋንቋ ተጠቅመን «ልዩ የሚያደረገዉ» ብንል ከቀዳሚዎቹ የሚለይበትን ብዙ «ልዩዎች» መዘርዘሩ አይገድም።ጉዳያችን ግን ምርጫዉ ከዝግጅቱ-እስከ ዉጤቱ ባለዉና በሚኖረዉ ሒደት ኢትዮጵያዉን ጋዜጠኞች የሚዘግቡ ወይም የማይዘግቡበትን ሰበብ፤ ምክንያት እና ሑነት ባጭሩ መቃኘትነዉ።ሥለዚሕም ምርጫዉ «ልዩ» የሚሆንበትን ምክንያት ስናወሳ-የምናነሳዉ ከጋዜጠኞች፤ ከመገናኝ ዘዴዎች ነጻነትና በነፃነት ከመዘገብ ጋር የተያያዘዉን ብቻ ነዉ።

እንግዶቻችን በሙሉ ጋዜጠኞች ሥለሆኑ ማንነታቸዉን ባጭጭሩ ያስተዋዉቁንና ዉይይታችንን ከዚሁ «ልዩ» ከሚሆንበት ጥያቄ እንጀምር።እንግዶቻችን በዉይይቱ ለመሳተፍ ፈቃደኛ በመሆናችሁ አመሰግናለሁ።

ነጋሽ መሐመድ

ማንተጋፍቶት ስለሺ