የኢትዮጵያ ምርጥ ዘር ድርጅት ስጋት18 ግንቦት 2003ሐሙስ፣ ግንቦት 18 2003የኢትዮጵያ ምርጥ ዘር ድርጅት የምርጥ ዘር ስርጭት ችግር እንዳጋጠመው አስታወቀ ። ድርጅቱ እንደሚለው በተለይ በቂ የተዳቀለ በቆሎ ዘር የተዘጋጀ ቢሆንም አርሶ አደሩ የሚጠበቀውን ያህል አልተጠቀመበትም ።https://p.dw.com/p/RQCuምስል CC /Anne Wangalachi/ CIMMYTማስታወቂያይህም በመጪው ዘመን ምርት መጠን ላይ ተፅዕኖ ሊያሳድር እንደሚችል ይገመታል ። የድርጅቱ ስራ አስኪያጅ ዶክተር ታፈሰ ገብሩ ለዴቼቬለ እንዳስረዱት ዘንድሮ ዝናቡ ከወትሮው በመዘግየቱና በመቆራረጡ ገበሬው ዘሩ ፍሬ ላያሰጥ ይችላል በሚል ስጋት የተዘጋጀውን ምርጥ ዘር ከመጠቀም ተቆጥቧል ። ዝርዝሩን ጌታቸው ተድላ ከአዲስ አበባ ልኮልናል ። ሂሩት መለሰ ጌታቸው ተድላ ነጋሽ መሐመድ