የኢትዮጵያ መንግስት እና የኦብነግ ቅድመ ድርድር
ሰኞ፣ ጳጉሜን 5 2004ማስታወቂያ
ለ28 ዓመታት የኦጋደን ክልልን ነጻ ለማውጣት የደፈጣ ውጊያ ሲካሂድ የቆየው የኦጋዴን ብሔራዊ ነጻ አውጪ ግንባር (ኦብነግ)ባለፈው ሳምንት ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር ለመደራደር በመሰራታዊ መርሆች ላይ ናይሮቢ ኬኒያ ውስጥ መስማማቱ ተሰምቷል። ድርድሩ ለሁለቱም አካላት ተስፋ ሰጪ እንደሚሆን ፤ የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ለዶቼቬለ ተናግረዋል ። ገመቹ በቀለ አነጋግራቸዋል። እንዲሁም ኦብነግ በቅድመ ድርድሩ ላይ ያለውን አስተያየት- አቶ ሀሰን አብዱላሂ -የኦብነግ የውጭ ጉዳይ ኮሚቴ እና የኢትዮጵያ ጉዳይ ኋላፊ ከለንደኑ ዘጋቢያችን ድልነሳው ጌታነህ ጋ ተነጋግረዋል። ዘገባዎቹን ማድመጥ ይችላሉ።
ገመቹ በቀለ
ድልነሳው ጌታነህ
ልደት አበበ
ሒሩት መለሰ