የኢትዮጵያ ህዝቦች የጋራ የትግል ሸንጎ ሥብሰባ
ሰኞ፣ ታኅሣሥ 22 2005ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ ህዝቦች የጋራ የትግል ሸንጎ የተሰኘ ድርጅት ትናንት እሁድ ለንደን ብሪታኒያ ስብሰባ አካዷል ። ሸንጎው ከተመሰረተ ወዲህ ለንደን ውስጥ ስብሰባ ሲያደርግ የእሁዱ የመጀመሪያው ነው ። ድርጅቱ እንደሚለው አላማው በኢትዮጵያ የዘረኝነትን ስርዓት ለማስወገድ የተረጋጋ ህዝባዊ ዲሞክራሲያዊ ስርዓት ዕውን ማድረግ ነው ። በድርጅቱ እምነት ይህን ለማሳካት የፖለቲካ ድርጅቶች ብቻ ሳይሆኑ ዜጎች በጋራ መንቀሳቀስ ይኖርባቸዋል ። ሃና ደምሴ ከለንደን ዝርዝሩን ልካልናለች።
ሃና ደምሴ
ሂሩት መለሰ
ሸዋዬ ለገሠ