የኢትዮጵያው አውሮፕላን አደጋ መንስኤ እስካሁን አለመታወቁ
ረቡዕ፣ ጥር 26 2002ማስታወቂያ
ከአስር ቀን በፊት አየር ላይ ተበታትኖ ሜዲትራንያን ባህር ላይ የወደቀው የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን ለአደጋ የተጋለጠበት ምክንያት እስከሁን ድረስ በውል አልታወቀም ። የአውሮፕላኑን የአደጋ መረጃ መሰብሰቢያ መሳሪያ ማለትም ብላክ ቦክስ ለማግኘት የሚደረገው ፍለጋም እንደቀጠለ ነው ። እስካሁን ድረስ አውሮፕላኑ አስፍሯቸው ከነበሩት ሰዎች ውስጥ የተገኘው አስከሬን አስራ አምስት ብቻ ነው ። የሟቾቹን ማንነት ለመለየት ከወላጅ ዘመዶቻቸው ላይ የምርመራ ናሙና ተወስዷል ። ነጋሽ መሀመድ አደጋውን የሚከታተለው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ልዩ ግብረ ኃይል አስተባባሪ ካፒቴን ደስታ ዘርዑን በስልክ አነጋግሯቸዋል ።
Interv.Cap.Desta Zeru
Negash Mohammed