የኢትዮጵያውያን የስደት አዙሪትና መፍትሄው
እሑድ፣ ሐምሌ 19 2007ማስታወቂያ
ውጊያ በሚካሄድባት የመን የሚገኙ ኢትዮጵያውያንን የማስወጣቱ ስራ ቀጥሏል ።የኢትዮጵያ መንግሥት ና ዓለም ዓቀፉ የስደተኞች ጉዳይ ድርጅት IOM እስካሁን 5871 ኢትዮጵያውያንን ወደ ሃገራቸው መመለሳቸው ተዘግቧል ።በሌላ በኩል ኢትዮጵያውያኑን ወደ ሃገራቸው የመመለሱ ጥረት በቀጠለበት በአሁኑ ጊዜ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች በአደገኛ የባህር ጉዞ ለመጀመሪያ ጊዜ እንዲሁም እንደገና እየተመለሱ የመን እየገቡ ነው ። ከመካከላቸው ከዚህ ቀደም ወደ ተባረሩበት ወደ ሳውዲ አረቢያ ለመሄድ የሚጠባ በቁም ይገኙበታል ። ኢትዮጵያውያን ስደተኞችን ከየመን የመመለሱ ጥረትና የኢትዮጵያውያን የስደት አዙሪት የዛሬው እንወያይ የመነጋገሪያ ርዕስ ነው ።
ኂሩት መለሰ
አዜብ ታደሰ