የኢትዮጵያውያን ስደትና መፍትሔዎቹ
እሑድ፣ ሚያዝያ 13 2005ማስታወቂያ
የኢትዮጵያውን ስደተኞች ቁጥር እየጨመረ በመሄድ ላይ ባለበት በአሁኑጊዜ በየሄዱበት የሚገጥሟቸው ችግሮችም የዚያኑ ያህል ከፍ ብለዋል ። በተለይ ወደ ጎረቤት ና አረብ ሃገራት የሚሰደዱት በጉዞ ወቅት እንዲሁም በተሰደዱባቸው አካባቢዎች እጅግ ዘግናኝ በደሎች እንደሚፈፀሙባቸው በተለያዩ አጋጣሚዎች ይናገራሉ ። ለተሻለ ህይወት ሃገር ጥለው ወጥተው ፣ እንደ እቃ በደላሎች የሚሸጡ ፣ ገንዘብ ካላመጣችሁ እየተባሉ የሰውነት አካላቶቻቸው ላይ ጉዳት የሚደርስባቸው ፣ የሚገደሉ ፣ የግድያ ዛቻ የሚሰነዘርባቸው ቁጥር ቀላል አይደለም ። ህገ ወጥ እየተባሉ በባዕድ ሃገር እስር ቤቶች የሚሰቃዩትም እንዲሁ በርካታ ናቸው ። እየተባባሰ የሄደው የኢትዮጵያውያን ስደትና መፍትሔዎቹ የእንወያይ የመነጋገሪያ ርዕሰ ነው ።
ሂሩት መለሰ
ማንተጋፍቶት ስለሺ