የኢትዮጵያውያን ሕዝባዊ ስብሰባ በፍርንክፈርት
ሰኞ፣ ሚያዝያ 26 2007ማስታወቂያ
የስብሰባው ሥርዓት የተከፈተው በቅርቡ በሊቢያ፤ በደቡብ አፍሪቃና በየመን በአሠቃቂ ሁኔታ ሕይወታቸውን ላጡ ኢትዮጵያውያን የሕሊና ጸሎት በማድረግ ነው። ንግግር ያሰሙት ተጋባዥ እንግዶች፤ ኢትዮጵያውያን በዓለም ዙሪያ ፤ ወዳጆች፤ አጋዦች እንደሌላቸው በአጽንዖት ከማስገንዘባቸውም፤ ወቅቱ፤ ኢትዮጵያውያን ሁሉ፣ ልክ እንደ አንድ ቤተሰብ ፤ በአንድነት፣ በፍቅር እንዲቆሙ የሚገፋፋ አማራጭ የሌለው ዐቢይ ጉዳይ ነው ብለዋል። በስብሰባው ተገኝቶ የነበረው ጎይቶም ቢሆን ተከታዩን ዘገባ ልኮልናል።
ጎይቶም ቢሆን
ተክሌ የኋላ