1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኢትዮጵያውያን ሐጃጆች ችግር

ማክሰኞ፣ ታኅሣሥ 5 2003

ለዘንድሮው የሐጂ ፀሎት ወደ መካና መዲና ሳዑዲ አረቢያ የተጓዙ ኢትዮጵያውያን የእስልምና ዕምነት ተከታዮች እስካሁን ድረስ ወደ ሐገራቸው ባለመመለሳቸው ለከፍተኛ ችግር መጋላጣቸውን አስታወቁ ።

https://p.dw.com/p/QYbV
ምስል AP
ምዕመናኑ እንደሚሉት ጉዞአቸውን ለሚያስተናብረው ለኢትዮጵያ የሐጂ ኮሚቴ የሚፈለግባቸውን የመስተንግዶና የደርሶ መልስ የአውሮፕላን ቲኬት ውጪ ቢከፍሉም መመለስ በሚገባቸው ጊዜ ወደ ሐገራቸው መመለስ አልቻሉም ። የሐጂ ኮሚቴው በሚታየው የአሰራርና የቅንጅት ጉድለት ምክንያት በየዓመቱ ለፀሎት ወደ ሐጂ የሚጓዙ ምዕመናን ለከፍተኛ ችግር ይዳረጋሉ ። የጂዳው ወኪላችን ነብዩ ሲራክ ጉዳዩን ተከታትሎታል ነብዩ ሲራክ ተክሌ የኋላ ሂሩት መለሰ