የኢትዮጵያውያንና ኤርትራውያን ስደተኞች ይዞታ
ማክሰኞ፣ ግንቦት 9 2003ማስታወቂያ
ብዙዎቹ ወደ ጎረቤት ሀገራት ግብፅ እና ቱኒዝያ የሄዱ ሲሆን ፤ እድል ቀንቷቸው ከአስቸጋሪው ሁኔታ ያመለጡት በሺህዎች የሚቆጠሩት ደግሞ የሜዲቴራንያንን ባህር በጀልባዎች አቋርጠው ወደ ኢጣልያዋ ደሴት ላምፔዱዛ እና ወደ ሌሌላኛ ደሴት ማልታ መግባት ችለዋል ።ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ ደግሞ በጉዞ ላይ የውሐ ሲሳይ ሆነው መቅረታቸው በየጊዜው እየተዘገበ ነው ። ከአደገኛ የባህር ላዩ ጉዞ ተርፈው ወደ ነዚህ ደሴቶች ከገቡት ውስጥ በሺህዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያንና ኤርትራውያን ስደተኞች ይገኙበታል ። እነዚህ ስደተኞች በደረሰቡቸው የአውሮፓ አገራት በምን ዓይነት ሁኔታ ላይ ይገኛሉ ? የወደፊቱስ እጣቸው ምን ይሆን ? የዛሬው አውሮፓ እና ጀርመን ዝግጅታችን ትኩረት ነው ።
ሒሩት መለሰ
ነጋሽ መሐመድ