1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኢትዮጵያዉያን ቤተእስራኤላዉያን

ሰኞ፣ የካቲት 11 2005

ከሰላሳ ዓመታት በፊት እስራኤል ያካሄደችዉ ቤተእስራኤላዉያንን ከኢትዮጵያ የማዉጣት ዘመቻ ብዙዎቹን ወደሚያልሟት ምድር ማድረሱ ቢታመንም በሂደቱ ያለፉ ወገኖች ጉዳይ ሲያነጋግር ቆይቷል።

https://p.dw.com/p/17gQR
ምስል picture-alliance/dpa

የሀገሪቱ መንግስት ቤተእስራኤላዉያኑን መጀመሪያ በመርከብ በመቀጠልም በአየር ያጓጓዘ ሲሆን አስቸጋሪዉን የእግር ጉዞ አጠናቀዉ በሱዳን በኩል እስራኤል የገቡት በብዙ ሺህ ይገመታሉ። እነዚህ ወገኖች ምድረ እስራኤል እስኪደርሱ በጉዞ እንግልት እንዲሁም ሱዳን ዉስጥ በመጠለያ ጣቢያ በተነሳ ወረርሽኝ ያንዳንዶቹን ህይወት ማሳጣቱ ተሰምቷል። በወቅቱ ካሰቡበት ሳይደርሱ በመንገድ የቀሩትን ቁጥር ለማወቅ ምዝገባ ተጀምሯል። እስራኤል ሃይፋ የሚገኘዉ ወኪላችን ግርማዉ አሻግሬ ዝርዝር ዘገባ ልኮልናል።

ግርማዉ አሻሬ

ሸዋዬ ለገሠ

አርያም ተክሌ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ