የኢትዮጵያዉያን መገደልና የሐገሪቱ ምክር ቤት13 ሚያዝያ 2007ማክሰኞ፣ ሚያዝያ 13 2007የኢትዮጵያ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሊቢያና ደቡብ አፍሪቃ ዉስጥ ሰሞኑን በግፍ የተገደሉ ኢትዮጵያዉያንን ለማሰብ የሠወስት ቀን ብሕራዊ ሐዘን አወጀ።ምክር ቤቱ ዛሬ ባደረገዉ ሥብሰባዉ በሁለቱም ሥፍራዎች የተፈፀሙትን ግድያዎች አጥብቆ አዉግዟል።https://p.dw.com/p/1FC2kምስል DWማስታወቂያ የምክር ቤቱ እንደራሴዎች በየተራ ባሰሙት ንግግር «አይ ኤስ» የተሰኘዉ አሸባሪ ድርጅት የገደላቸዉንም ሆነ ደቡብ አፍሪቃ ዉስጥ የተገደሉትን ኢትዮጵያዉያን ቤተሰቦችን መንግሥት ሊያፅናናቸዉና ሊደግፋቸዉ ይገባል። ምክር ቤቱ ዛሬ ባሰለፈዉ ዉሳኔ መሠረት ከነገ-ጀምሮ ባንዲሮች በግማሽ ሠንደቅ ይዉለበለባሉ። ጌታቸዉ ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ ነጋሽ መሀመድ ሂሩት መለሰ