1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኢትዮጵያዉያን ሁኔታ በሳዑዲ

ሰኞ፣ ታኅሣሥ 14 2006

በስዑድ አረቢያ ወደ80 ሺህ የሚገመቱ ኢትዮጵያዉያን እጃቸዉን በሰላም እየሰጡ ወደሀገራቸዉ እንዲመለሱ መጠየቁ እየተነገረ ነዉ። ከጄዳ ቆንስላ እንደተነገረ የተጠቀሰዉን ማሳሰቢያ አስመልክቶ ማብራሪያ እንዲሰጡን ወደቆንስላዉ ባለስልጣናት ያደረግነዉ ተደጋጋሚ የስልክ ጥሪ ምላሽ አላገኘም።

https://p.dw.com/p/1Ag6x
ምስል AFP/Getty Images

በጂዳ የዶቼ ቬለ ዘጋቢ ነብዩ ሲራክ እንደሚለዉ የሳዉዲ መንግስት ሕጋዊ የመኖሪያ ፈቃድ የሌላቸዉ የዉጭ ዜጎች ከሀገሩ እንዲወጡ የጀመረዉ ዘመቻ ተጠናክሯል። ቆንስላዉ አስተላለፈ የተባለዉን ማሳሰቢያ አስመልክቶ ማብራሪያ እንዲሰጡት የዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲን በአጭሩ ጠይቀናል፣

Äthiopische Flüchtlinge in Saudi
ምስል Nebiyu Sirak

እንደየጂዳዉ ዘጋቢያችን ነብዩ ሲራክ ከሆነ ወደሳዑዲ በባህር፤ በሃጅና ኡምራ፤ በጉብንትና በሕጋዊ የመኖሪያ ፈቃድ የገቡት ኢትዮጵያዉያን ቁጥር ይህን ያህል ነዉ ብሎ ለመናገር ለጊዜዉ ያዳግታል። በጥብቅይተገበራልተብሎየሚጠበቀዉ የሳውዲሕግ ሕጋዊ የመኖሪያ ፈቃድ የሌላቸዉን ብቻ የሚመለከት አይደለም። ሕጋዊ መኖሪያ ፈቃድ ይዞ ከአሰሪው ጋር የማይሠራ ከሃገር ይውጣ መባሉ ሌላዉ የስጋት ምንጭ ሆኗል። ስለሁኔታዉ እንዲያብራራልን ነብዩን ስቱዲዮ ከመግባቴ አስቀድሜ በስልክ ጠይቄዋለሁ፤

ነቢዩ ሲራክ

ሸዋዬ ለገሠ

ኂሩት መለሰ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ