የኢትዮጵያን ወጣቶች የሚፈታተነው ስራ አጥነት
ዓርብ፣ ሚያዝያ 16 2007ማስታወቂያ
በአሁኑ ወቅት ከኢትዮጵያ ወደ ሊቢያ፣ደቡብ አፍሪቃ ፣የመን እና የመካከለኛው ምስራቅ ሀገራት የተሰደዱ ወጣቶች ለሞት፣ እንግልት እና ስቃይ ይዳረጋሉ። ብዙዎቹ ከሀገራቸው የሚሰደዱት ለተሻለ የስራ እድል እና የኑሮ ፍለጋ ነው። ስደቱ አሁንም አላቆመም።
በአሁኑ ወቅት በርካታ የተማሩም ይሆን ያልተማሩ ኢትዮጵያዊያን ወጣቶች ኑሮዋቸውን ለማሻሻል ከሀገር መውጣትን እንደ ብቸኛ አማራጭ ሲቆጥሩ ተስተውሏል። ለዚህም ስደት በዋና ምክንያትነት የሚጠቀሰው በኢትዮጵያ ያለው ስራ አጥነት ነው።
የኢትዮጵያ መንግሥት የስራ አጡ ቁጥር ካለፉት አመታት ጋር ሲነፃጸር መቀነሱን ቢገልፅም በርካታ ተመራቂ ወጣቶች በተመረቁበት መስክ ስራ አያገኙም። ዳውድ ተምረው ስራ ካጡት ኢትዮጵያውያን ወጣቶች ተርታ ይሰለፋል። «ትምህርት መማሬ አልጠቀመኝም» ይላል። ለዛሬ፤ ስራ የያዙ፣ ስራ የሌላቸው እና በቅርቡ የስራውን ዓለም ለመቀላቀል በዝግጅት ላይ ያሉ ወጣቶች ተሞክሮዋቸውን ያካፍሉናል። ዘገባውን በድምፅ ያገኙታል።
ልደት አበበ
ሂሩት መለሰ