1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኢትዮጵያና የኤርትራ ጉዳይ ስብሰባ

ማክሰኞ፣ መጋቢት 20 2003

የኢትዮ-ኤርትራ አለም አቀፍ የወዳጅነት ጉባኤ ተካፋዮች እንዳሉት የሁለቱ ሐገራት ሕዝቦች ወደ ጠብና ግጭት የሚያመሯቸዉን ችግሮች በጋራ ለማስወገድ መጣር አለባቸዉ።

https://p.dw.com/p/RDiW
የኢትዮጵያና የኤርትራ ጉዳይ ስብሰባ

የኢትዮጵያና የኤርትራ ሕዝቦች መልካም ወዳጅነትና ግንኙነት ለመመስረት እንዲጥሩ የሁለቱ ሐገራት ምሁራንና የመብት ተሟጋቾች ጠየቁ።ሳንሆዜ-ዩናይትድ ስቴትስ ዉስጥ ተሰይሞ የነበረዉ የኢትዮ-ኤርትራ አለም አቀፍ የወዳጅነት ጉባኤ ተካፋዮች እንዳሉት የሁለቱ ሐገራት ሕዝቦች ወደ ጠብና ግጭት የሚያመሯቸዉን ችግሮች በጋራ ለማስወገድ መጣር አለባቸዉ።ጉባኤተኞቹ እንደሚሉት በሁለቱ ሐገራት መካካል እስካሁን የተደረጉ ጦርነቶችም በመንግሥታት ወይም በመሪዎች እንጂ በሁለቱ ሕዝቦች ፍላጎት የተደረጉ አይደሉም።የዋሽንግተኑ ወኪላችን አበበ ፈለቀ ዝር ዝር ዘገባ ልኮልናል።

አበበ ፈለቀ

ነጋሽ መሐመድ

ተክሌ የኋላ