1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኢትዮጵያና የኤርትራ የካሳ ኮሚሽን ዉሳኔና የባለሙያ አስተያየት

ረቡዕ፣ ነሐሴ 13 2001

በታላቋ ብሪታንያ የደንዲ ዩኒቨርስቲ የሕግ ፕሮፌሰር መላኩ ገቦዬ እንደሚሉት ትናንት ይፋ የሆነዉ የካሳ ዉሳኔም ሆነ ከዚህ ቀደም የተላለፈዉ የድንበር አካላይ ኮሚሽን ዉሳኔ ገቢር ለመሆን ብዙ ጊዜ ይጠይቃሉ።

https://p.dw.com/p/JEK1
በጦርነቱ ከወደሙት አካባቢዎች አንዱምስል AP

የኢትዮጵያና የኤርትራን የድንበር ዉዝግብ በተመለከተ የተላለፉት ዉሳኔዎች የወደፊት ግንኙነት ላይ ከፍተኛ ተፅዕኖ እንደሚኖረዉ አንድ የአለም አቀፍ ሕግ ባለሙያ አስታወቁ።በታላቋ ብሪታንያ የደንዲ ዩኒቨርስቲ የሕግ ፕሮፌሰር መላኩ ገቦዬ እንደሚሉት ትናንት ይፋ የሆነዉ የካሳ ዉሳኔም ሆነ ከዚህ ቀደም የተላለፈዉ የድንበር አካላይ ኮሚሽን ዉሳኔ ገቢር ለመሆን ብዙ ጊዜ ይጠይቃሉ።ዉሳኔዎቹ በወደፊቱ የሁለቱ ሐገሮች ግንኙነት ላይ የሚኖራቸዉ ተፅዕኖ ግን እንደባለሙያዉ እምነት ከፍተኛ ነዉ።የብራስልሱ ወኪላችን ገበያዉ ንጉሴ ዶክተር መላኩን አነጋግሮ-የሚከተለዉ ዘገባ ልኮልናል።

ገበያዉ ንጉሴ /ነጋሸ መሀመድ

አርያም ተክሌ