1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኢትዮጵያና የቱርክ ግንኙነት

እሑድ፣ የካቲት 27 1997

የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚንስትር አቶ መለስ ዜናዊ፧ ከቱርኩ አቻቸው ሪቸፕ ታዪፕ ኤርዶጋን ጋር በተለያዩ ረድፎች ለመተባበር ከተስማሙ በኋላ፧ በ፪ ቱ አገሮች መካከል ወታደራዊ ግንኙነትን የማጠናከር ፍላጎት ያላቸው መሆኑን፧ አስታወቁ።

https://p.dw.com/p/E0kE

ከእንግዳቸው ጋር በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ፧ ኢትዮጵያ፧ በጦር መሣሪያ ግዢ ዘመቻ ላይ እንደማትገኝና የራሷ የመከለከያ ኢንዱስትሪ እንዳላት በመጥቀስ፧ ከቱርክ ጋር በዚህ ረገድ መተባበር የሚቻልበትን ሁኔታ እንደሚመረምሩ ገልጸዋል። የቱርክ ጠቅላይ ሚንስትር ኤርዶጋን፧ በአፍሪቃ ዋንኛ የንግድ ተባኣቢዋ ወደሆነችው ደቡብ አፍሪቃ ከማምራታቸው በፊት በሰጡት መግለጫ፧ በጨርቃ-ጨርቅ ቆዳና ሌጦ፧ በመከላከያ ኢንዱስትሪ ዘርፍ፧ እንዲሁም በኃይል ምንጭ ረገድ፧ አገራቸው ከኢትዮጵያ ጋር የመተባበር ፍላጎት ያላት መሆኑን አስታውቀዋል። የኢትዮጵያና የቱርክ የአሁኑ ዓመታዊ የንግድ ልውውጥ መጠን፧ በ፻ ሚልዮን ዶላር የሚገመት ሲሆን፧ ኤርዶጋን ወደ ፭፻ ሚልዮን ዶላር ከፍ እንዲል ለመድረግ የሚጥሩ መሆናቸውን አመልክተዋል።