1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኢትዮዽያ ብር ከዶላር አንጻር ዋጋው በ17 በመቶ ቀነሰ

ሐሙስ፣ ነሐሴ 27 2002

የዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም አይ ኤም ኤፍ ውሳኔው አወድሶታል። የኢኮኖሚው ባለሙያዎች ግን ለኢትዮዽያ አደገኛ የሆነ ውሳኔ ብለውታል።

https://p.dw.com/p/P2aE
1 ዶላር 16ብር ከ35ሳንቲም ገባምስል AP Graphics

የኢትዮዽያ መንግስት የብርን የመግዛት አቅም በ17 በመቶ ዝቅ እንዲል ያደረገ ውሳኔ ትላንት አስተላልፏል። መንግስት ይህን ውሳኔ ያስተላለፈበትን ምክንያት በዝርዝር አልገለጸም። በዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም የኢትዮዽያ ተወካይ፤ ኢትዮዽያ ወደውጭ በምትልካቸው ምርቶች ተወዳዳሪነቷን የሚያሳድግ ውሳኔ ሲሉ ገልጸዋል። ይህ በብር የመግዛት አቅም ላይ በከፍተኛ መጠን ዝቅ እንዲል የተደረገበት ውሳኔ በኢኮኖሚ ባለሙያዎች ዘንድ የተለያዩ አስተያየቶች አየተሰጡበት ነው። በቺካጎ ሀርቨር ኮሌጅ የኢኮኖሚክስ መምህር ፕሮፌሰር ጌታቸው በጋሻው ከዓለም ዓቀፍ ባንክና ከገንዘብ ተቋማት በተደረገ ግፊት መንግስት እርምጃውን ወስዷል ሲሉ ይናገራሉ። ይህ እርምጃ ግሽበትን የሚያባብስ፤ የኢኮኖሚውን ቀውስ የሚያጠናክር፤ ደሀውን ህዝብ የበለጠ የሚጎዳ ነው ብለዋል--ፕሮፌሰር ጌታቸው።

መሳይ መኮንን

ሂሩት መለሠ

ሸዋዬ ለገሠ