የኢራፓ ጥያቄ
ረቡዕ፣ ጥቅምት 8 2010ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ ገዢ ፓርቲ ኢሕአዴግ ሠላማዊ የሥልጣን ሽሽግግር ለማድረግ እንዲዘጋጅ የኢትዮጵያ ራዕይ ፓርቲ የተሰኘዉ ተቃዋሚ የፖለቲካ ማሕበር ጠየቀ።ኢራፓ በሚል ምሕፃረ ቃል የሚጠራዉ ተቃዋሚ ፓርቲ ማዕከላዊ ኮሚቴ ባወጣዉ መግለጫ እንዳለዉ የኢትዮጵያ ሕዝብ የሥልጣን ሽግግር እንዲደረግ እየጠየቀ ነዉ።ፓርቲዉ ጥያቄዉን እንደሚያምንበት አስታዉቆ ኢሕአዴግም የሕዝብን ጥያቄ ተቀብሎ ለሥልጣን ሽግግር እንዲዘጋጅ አሳስቧል።
ጌታቸዉ ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ
ነጋሽ መሐመድ
ኂሩት መለሰ