1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኢራን እና ስዑዲ ዓረቢያ ውዝግብ

ረቡዕ፣ ታኅሣሥ 27 2008

የስዑዲ አረቢያ እና የኢራን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት መቋረጥን ተከትሎ ባሕሬን እና ሱዳን የስዑዲን ፈለግ ተከትለው ከኢራን ጋር ግንኙነት አቋርጠዋል። ሌሎች ሃገራትም የኢራንን ድርጊት አውግዘዋል። የግንኙነት መቋረጡ እና የውግዘቱ ዳራ የብዙ ዓመታት መቆራቆዝ ውጤት እንደሆነ ቢነገርም፤ ስዑዲ ዓረቢያ የሺዓ ሃይማኖታዊ መሪ ሼሕ ኒምር አል ኒምርን

https://p.dw.com/p/1HZL7
Iran Protest in Teheran gegen Hinrichtung in Saudi-Arabien
ምስል picture-alliance/AP Photo/V. Salemi

[No title]

በሞት መቅጣቷ የፈጠረው ቁጣ ነገሩን እንዳጦዘው ተገልጧል።የሼሕ ኒምር አል ኒምር በስዑዲ ዓረቢያ በሞት መቀጣት የኢራንን ሕዝብ አስቆጥቶ አደባባይ እንዳስወጣው ይታወሳል። ያም ብቻ አይደለም ሕዝቡ በመዲናዪቱ ቴሕራን የሚገኘው የስዑዲ አረቢያ ኤምባሲ ቅጥር ግቢን በእሳት መለኮሱ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነቱ እንዲቋረጥ ሰበብ ተደርጎ ይወሰዳል። በእርግጥ በስዑዲ ዓረቢያ እና ኢራን መካከል በአካባቢው ተሰሚነትን ለማግኘት የሚደረግ ፉክክር ቢኖርም ማለት ነው። የኢራን እና ስዑዲ ዓረቢያ ውጥረትን በተመለከተ የጂዳ ተባባሪ ዘጋቢያችን ነቢዩ ሲራክን በሥልክ አነጋግሬዋለሁ። የሁለቱ ሃገራት ግንኙነት መቋረጥን ተከትሎ የሌሎች ሃገራት ውሳኔ ምን እንደሚመስል በመተንተን ይጀምራል።

ነቢዩ ሲራክ

ማንተጋፍቶት ስለሺ

ነጋሽ መሐመድ