የኢሕአዴግ አባል ፓርቲዎች ጉባኤ
ረቡዕ፣ ነሐሴ 20 2007ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ ገዢ ፓርቲ የኢሕአዴግ ተጣማሪ ፓርቲዎች በየአካባቢያቸዉ የየራሳቸዉን ጉባኤ እያደረጉ ነዉ።ከአራቱ ፓርቲዎች ቀደም ብሎ ጉባኤዉን ያገባደደዉ የደቡብ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ደሕዴግ) ጠቅላይ ሚንስትር ሐይለ ማርያም ደሳለኝን የፓርቲዉ ሊቀመንበር አድርጎ በድጋሚ መርጧቸዋል።የግንባሩን መሥራች ዶክተር ካሱ ኢላላን ደግሞ አሰንብቷል።የብሔረ አማራ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ብአዴን) በበኩሉ የቀድሞዉን የፓርቲዉን ሊቀመንበር አቶ አዲሱ ለገሠን ጨምሮ ቢያንስ ሠወስት ነባር ባለሥልጣናቱን አሰናብቷል።የኦሮሞ ሕዝብ ዴሞክራሲዊ ድርጅት (ኦሕዴድ) እና የሕዝባዊ ወያኔ ሐርነት ትግራይ (ሕወሐት) ጉባኤዎች ነገ ይጠናቀቃሉ ተብሎ ይጠበቃል።የአዲስ አበባዉ ወኪላችን ዮሐንስ ገብረ እግዚ አብሔር ዝርዝር ዘገባ ልኮልናል።